በህውሀት የሚመራው መንግስት ያስጀመረውና ያቀጣጠለው ውዝግብ ወደ አጠቃላይ ቀውስ ሊያመራ ከሚችልበት ጫፍ ላይ ደርሷል።

(መሳይ መኮንን) — በህውሀት የሚመራው መንግስት ያስጀመረውና ያቀጣጠለው ውዝግብ ወደ አጠቃላይ ቀውስ ሊያመራ ከሚችልበት ጫፍ ላይ ደርሷል። የሶማሌ ልዩ ሃይል በህወሀት የተዘጋጀውን የአጥፍቶ መጥፋት ፕሮጄክት ሊያስፈጽም በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ዘምቷል። የታላቋ ሶማሊያ ምስረታን ለማስፈጸም ከሞቃዲሾ የተዘረጋ የድብቅ ወረራ አጀንዳ አድርገው ለሚያራግቡ ሰዎች ጆሮ ነፍገን የህወሀትን እንቅስቃሴ በጥሞና መከታተልና መታገል የሚያዋጣ ይመስላል። ህወሀት የበተነውና ችግሩን ወደሌላው ለማላከክ ያሰራጨው ‘የታላቋ ሶማሊያ’ ወሬ ገለባ ነው። ያላቸውን መሰብሰብ ያልቻሉት ሶማሊያውያን ሌላ መሬት ወረራ ይፈጽማሉ ብሎ መነሳት አንድም አላዋቂነት ነው ወይም መሰሪነት ነው። በኦሮሞ ወገናችን ላይ የሚደረገውን ለከት ያጣ የወረራና ግድያ እርምጃ ከምንጊዜውም በላይ ልንታገልው የሚገባ ሲሆን በቄሮዎች የተላለፈውን ጥሪ በመቀበል የህወሀትን ድብቅ አጀንዳ ማክሸፍ ግድ ይላል።ኢትዮጵያን በምስራቁ በሯ በጽኑ አሟታል።
-በጎንደር ህወሀት የቀበረው ፈንጂ ሊፈነዳ ጥቂት ቀናት ቀርቶታል። ጎንደር ጭንቅ ላይ ናት። ህወሀት ከመቀሌ ያሰማራቸው የምርጫ አስፈጻሚዎች ጎንደር ዙሪያ መግባታቸው እየተነገረ ነው። የቅማንት ካርድ ለጎንደር በአጠቃላይም ለኢትዮጵያ መከራ ሊያመጣ ከጫፍ የደረሰ ይመስላል። የህወሀት ሹማምንት ቅማንትን ከጎንደር ለመነጠል የቅማንትን ቆብ ደፍተው ተሰማርተዋል። አደጋው ከባድ ነው። የተቃወሙ እየታሰሩ ነው። ምርጫ የተባለው መስከረም ሰባት ተቃርቧል። ህወሀት ግጨውን ከገዱ እጅ ፈልቅቆ ከውሰደ በኋላ የሚቀረው የቅማንትን ፕሮጀክት መፈጸም ነው። ለዚያም ቀን ከሌሊት እየተሯሯጠ ነው።

መቋጠሪያው ሀሳብ

በህወሀት ጥብቆ ተለክቶ የተሰፋው የጎሳ ፌደራሊዝሙ ከሽፏል። The ethnic federalism is failed.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *