የዘር ፍጅት በጎንደር ህዝብ ላይ ለመፈጸም ማቀዳቸውን ሾልኮ የወጣው መረጃ ያመለክታል ።

ህወሃት/ በጎንደር ህዝብ የሚሸርበው የመከፋፈል ተንኮል አጥብቄ እቃወማለሁ፨ ቆርሶ ወደ ትግራይ ባጠቃለለው የወልቃይት ጠገዴ አማሮች ላይ ያካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተከትሎ መላው የአማራ ህዝብ በነቂስ “ወልቃይት ይመለስልን” የሚል ጥያቄ ማንሳቱ ይታወሳል ። በዚህም ምክንያት በርካታ አማሮች በጅምላ ቢጨፈጭፉም የአማራ ህዝብ አሁንም ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወያኔ ህዝቡ ላነሳው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ መቀሌ ላይ ቢሮ በከፈተላቸው የቅማንት ታጋይ ነን ባይ ተላላኪዎች አማካኝነት ሌላ ዙር የዘር ፍጅት በጎንደር ህዝብ ላይ ለመፈጸም ማቀዳቸውን ሾልኮ የወጣው መረጃ ያመለክታል ። በመሆኑም ይሄንን በቅማንት ስም የተጀመረው ጸረ አማራ አጀንዳ እንዲቆም ብሎም ወልቃይት ወደ ወገኑ እንዲመልስ እጠይቃለሁ ። በማን አለብኝነት ለሚፈጠር ማንኛውም የሰው ህይወት መጥፋት ህወሃትና ቅጥረኞቹ ሃላፊነቱን ሊወስዱ ይገባል እላለሁ ።  ከስንታየሁ ቸኮል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *