ወያኔ ቀማንትን ገንጥሎ ወደ ትግራይ ለመቀላቀ የቅማንት ነፃ አውጪ መቀሌ ላይ ጠፍጥፎ የሰራውን የቅማንት ነፃአውጪን ሰው አስተዋወቀ !!

የ“ቅማንት ነፃ አውጭው” ነጋ ጌጤ ጉዳይ
*********************************
ነጋ ጌጤ በአሁን ሰዓት “ጌታን ተቀብያለሁ ፖለቲካ አልፈልግም ብሎ” በአሜሪካ ውስጥ ተደብቆ ከልጁ ጋር እንደሚኖር መረጃ ደርሶኛል፡፡ ባለፈው ዓመት በቅማንት ጥያቄ ስም በጎንደር ውስጥ ለፈሰሰው ደም ቁጥር አንድ ተጠያቂ የሆነው ነጋ “ቅማንትን ነፃ እንዳወጣ አያቴ ንግርት ነግሮኛል” ሲል ከረሞ ነበር፡፡ ከዝያም “የቅማንት ታሪክ” የሚል ህዝብን ለጥላቻ የሚያነሳሳ መፅሃፍ ፅፎ በበረከት ስምኦን ስፖንሰርነት አሳትሞ ለመላው ቅማንት በድብቅ መፅሃፉን ሲያከፋፍል ከረመ፡፡
የመፅሃፉ ወሬ እየተሰማ ሲመጣም ሌላው አማራ መፅሃፉን አንብቦ እንዳይረዳ በገበያ ላይ እንዳይከፋፈል አደረገ፡፡ የቅማንት ነፃ አውጭ ኮሚቴንም አቋቁሞ ከሌሎች ባንዶች ጋር ወደ መቀሌ ሄዶ ከህውሃት ዘንድ “ከአማራ ነፃ መውጣት” የሚል ስልጠና ወስደው ተመለሱ፡፡ ተመልሰውም አንድ ቤተሰብ የሆነውን የጎንደር ቅማንት-አማራ አንዴ ከአዲግራት ነን፣ አንዴ ከኦሮሞ ነን፣ አንዴ ከግብፅ ነን፣ እያሉ ህዝቡን ግራ እያጋቡ በፈጠሩት ጭቅጭቅ ብዙ ደም መፋሰስ ሆነ፡፡
በግል ህይወቱም በመድሃኒት ቤቱ ህገወጥ ፅንስ ማስወረድ ከጨረሳቸው ህፃናት በተጨማሪም እናቶችም እንደሞቱበትና በዚህ ምክንያት በደርግ ዘመን ታስሮ እንደነበር ባለፈው ፅሁፌ ገልጫለሁ፡፡ እና የዚህ ሁሉ ሰው ደም በእጁ ላይ ያለ ሰው አሁን ተገለባብጦ “ጴንጤ ሆኛለሁ ፖለቲካ ትቻለሁ፣ ተውኝ” እያለ ነው፡፡
የአማራ ጠላቶች ሁሉ የህዝባችን ደም ሲያፈሱ ከከረሙ በኋላ ደም መላሽ ሲነሳ “ጌታን ተቀብያለሁ ማሩኝ” የሚሉት ፈሊጥ አይመቸኝም፡፡ ንስሃው የእውነት መሆኑን በምን ማወቅ ይቻላል? ታምራይ ላይኔ ትዝ አላችሁ?ታምራት እንኳን ወያኔዎች ቃሊቲ እስር ቤት በግብረሰዶም ደፍረውት የአእምሮውን ብሎን ካላሉት በኋላ መሰለኝ ፈገግ ብሎ የቀረው፡፡ ይኸኛውስ? ያፈሰሰው ደም በለሊት እየመጣ እንቅልፍ አሳጣው እንዳልል ሰውነቱ ደም የለመደ ህሊናውም የደነዘዘ ነው፡፡ ደም መላሽ እንደተነሳ ሰምቶ መሆን አለበት፡፡ ለማንኛውም እሱ አሜሪካ ቢደበቅ ቀሪ ቤተሰቡና ንብረቱ አሁንም ጎንደር ውስጥ ይገኛል፡፡ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *