ቴዲ ሐገር አለኝ ወገን አለኝ ብሎ የሚያምን አንድ ኢትዮጵያዊ እንጂ በማናችሁም ስርዓት ላይ ሸፍቶ ጦር ይዞ ዱር የከተተ ሽፍታ አይደለም።

እናንተ ያፈረሳችኋትን ኢትዮጵያን የገነባ፤ እናንተ ያቆሸሻችኋትን አቢሲኒያን ያፀዳ፤ እናንተ የከፋፈላችኋትን ቅድስት ሐገር አንድ ለማድረግ የጣረን ሰው እንደምን ትጣሉታላቹ…? ቴዲ ሐገር አለኝ ወገን አለኝ ብሎ የሚያምን አንድ ኢትዮጵያዊ እንጂ በማናችሁም ስርዓት ላይ ሸፍቶ ጦር ይዞ ዱር የከተተ ሽፍታ አይደለም። አንድ አብርሃምን የማያውቅ ንጉስ በግብፅ በነገሰ ጊዜ ህዝበ እስራኤልን መከራ አበዛበት ፈጣሪም ያን ህዝብ ከባርነት እና ከመክራ ታድጎ ከነዓንን አውርሶታል። ያን ሁሉ ህዝብ ባህር አሻግሮ መና ከሰማይ እያወረደ መግቦ ማር እና ወተት ወደምታፈልቀው ገናናዋ ሐገር ሲያደርሰው ለፈጣሪ ምንም አልከበደውም ነበር! አሁንም ለአንድ ቴዲ ሉዓላዊነት እና ነፃነት ያ የእስራኤል አምላክ አያንስም። ግፉን ይቆጥራል! በደሉን ያያል! ስቃይ እና ህመሙን ያስባል! የዛኔ በእጥፍ ይቀጣችኋል።

በባህላችን አንድ እንግዳ ጋብዞ መጥፋት ወይም መቅረት ትልቅ ነውር ነው። /ይሄን እንደማታውቁ ተስፋ አደርጋለው! ምክኒያቱም ጫካ ውስጥ ባህል እና ወግ አልነበረማ።/ ቴዲን ያን ባህል እንደጣሰ ለማስመሰል እና በሰው ፊት ለማሳፈር ይህን አደረጋቹ። ነገሩ ግን ወዲህ ነው። ከናንተ ጠባይ ለጠባይ ተግባብተን የለ ጥርጥሪያችኋለው። ልትከለክሉት እንደምትችሉ መገመት ለኛ ያን ያህል ከባድ አልነበረም። ዝምብ ጥሩ መዓዛ ባለበት ስፍራ መች ተገኝታ ታውቅ እና…? ግፋቹ በዚ አያበቃም ቴዲ በለም አቀፍ ደረጃ የገዘፈ አርቲስት ነው የውጪ ሚዲያዎች አምባገነንነታችሁን ያወጡታል። ያደፈ ጨርቃችሁን ለአለም ይገልጡታል።
ቴዲ ከመጀመሪያው ኮንሰርት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በልምምድ ላይ ነበረ! ከአስራ አምስት ቀን በላይ። ስራውን ወዳድ መሆኑ በዚህ ያስታውቃል። ስራውን የሚወድ ሰው ደሞ በፍትፁም ቶሎ ተስፋ አይቆርጥም። ቴዲን እናውቀዋለን ታውቁታላችሁም! እንኳንስ የአልበም ምረቃ ቀርቶ በሚሊየን በሚቆጠር ብር ኪሳራ ደርሶበት #ቀላል_ይሆናል የሚል እጅጉን ትግስተኛ ሰው ነው። ምናልባት አላማቹ እሱን አማሮ ከሐገር ማስወጣት ይሆናል…ቴዲ ግን ሰነፍ ሰው አይደለም። ያረጀች እናቱን ብቻዋን ጥሎ የሚሰደደ ልጅ እናቴን ልጦር ነው ቢል የሚጋጭ ነገር ነው የሚሆነው። ቴዲም ያረጀች እናቱን /ሐገሩን/ ጥሎ መሄድ፤ መሰደደ አይችልም።/እንደዛ ሰነፍ ሰው/ ስለዚህ ግፍ በላያቹ ከምታበዙ ብትተዉት የተሻለ ነው።
✎✍✍በ#ታሪኩ_ሐብታሙ®/ታታ/✔

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *