የህወሀት መንግስት የጥፋት ግስጋሴ በአስቸኳይ ካልተገታ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው ብሏል

(ኢሳት ዜና –ነሀሴ 24/2009) ኢትዮጵያ አደገኛ በሆነ አቅጣጫ እየተወሰደች በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ በስልጣን ላይ ያለውን ስርዓት ለማስወገድ መታገል ይኖርበታል ሲል የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ገለጸ። የኢትዮጵያ ለም መሬቶችን ለሱዳን ለ10ዓመታት በውሰት ለመስጠት በድብቅ ከስምምነት መደረሱን በመጥቀስ ጥሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ፡ የህወሀት መንግስት የጥፋት ግስጋሴ በአስቸኳይ ካልተገታ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው ብሏል። የታላቋን ትግራይ ካርታ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን በማሳየት ህዝቡ እንዲለማመደው እየተደረገ መሆኑና፡ ጎንደርን ለሶስት የመሸንሸኑ እርምጃ የዚሁ የታላቋ ትግራይ ምስረታ አካል ነው ብሏል የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *