ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ያለው አያሌው ጎበዜ ልማታዊ ዘራፊ እንደነበር ምንጮች ተናገሩ!!!

ጋሳ ሆቴል ፦ በቀበሌ 12 ከመናህሪያው በስተጀርባ
ይገኛል። በሽፋን ስም የጥቅም ተቋዳሽ በመሆን የተቀመጠው
ጋሻው ይባላል።
ጋሻው ከአመታት በፊት በሞጣ ሆስፒታል ሻይ ቤት ዳቦ ጋጋሪ
የነበረ ሲሆን ከቀድሞው የወያኔ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር
ከነበረው አያሌው ጎበዜ ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዳለው
ይታወቃል። ይህ ሆቴል ንብረትነቱ በአቶ አያሌው ጎበዜ
የቀድሞው የወያኔ የአማራ ክልል ር/መስተዳደር የነበረው ነው።
ሌሎችም አሉ እነትልቅ ሰው ገዳሙ መሰል ለሽፋን የተቀመጡ
ሰወች ብዙ ናቸው ። ይህንንም ጭቁኑ ህዝብ ያውቀዋል።
አውቆም ዝም አላለም ምቹ ቀን ይጠብቃል፤ ከህዝብ እየተዘረፈ
የተሰራ ነውና ንብረቱ የህዝብ ነው።
ከሰሞኑ እኒህንና ሌሎች የወያኔ ባለስልጣናት የስውር ንብረቶች
ላይ ጥቃት ይፈፀማል በሚል በፓፒረስ ሆቴል ስር በሚገኘው
የነዳጂ ማደያ ስምሪቱን በሚያደርግ ልዩ ሃይል ወታደር እና
በግሽ አባይ ክ/ከ ፅ/ቤት ውስጥ ሰፍሮ ባለ ልዩ ሃይል ታጣቂ
ጥብቅ ጥበቃ እየተደረገላቸው ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *