የወደፊቱ የgoogle ካርታ ጦርነት በኢትዮጵያ ‘

የወደፊቱ የgoogle ካርታ ጦርነት በኢትዮጵያ

ወዳጄ…የወደፊቱ የኢትዮጵያችን የካርታ ጦርነት ስልህ መቸም የካርታ ኮንከር ጌም ጨዋታ ነው ብለህ እንደማታስብ አስባለሁ፡፡ የካርታ ድምር ጌም ጨዋታም እያልኩህ አደለም፡፡ ወይንም “እያዩ ፈንገስ” እንዳለው ጨዋታው “በቤት ካርታም” አደለም፡፡በርግጥ የካርታ ጨዋታው የመደመርና መቀነስ አይነት ነው፡፡ ክፋቱ፣ ጨዋታው አንተና እኔ በልጅነታችን የለመድነውን አይነት የካርድ ካርታ ጨዋታ አይነት አደለም፡፡ ይህ የልጅነታችን ጌም ውርርዱ በቆርኪ፣ በቅጠል ብር ወይንም አደግ ካልክም ጨዋታው በሳንቲሞች ሊሆን ይችላል፡፡ ሆሆ…እንደዚህ ቢሆን እንዴት አሪፍ ነበር፡፡ ጌታው… የካርታ ጨዋታው ሙድ ተቀይሯል እኮ ነው የምልህ! ይባስ ይግረምህና …የጌሙ ዳኛም ተቀይሯል፡፡ በካርታው ጨዋታ ጌም አልስማማም ካልህ፣ ከፈለግህ ዳኝነትን ከ google map ፈልግ ነው የምትባለው፡፡

ይህን ሁሉ የማወራህ ለምን መሰለህ…The New York Times በ 2010 “The First Google Maps War” የተሰኘ ርዕስ በሰጠው ዘገባው በኒካራጉዋና ኮስታሪካ በተደረገ የድንበር “ጥሰሃል አልጣስኩም” ጥያቄ፣ የኒካራጉዋ የመንግስት ባለስልጣን የድንበር ውዝግቡን ለማሸነፍ፣ ከፈለጋችሁ ካርታውን google ላይ ፈልጋችሁ ማየት ትችላላችሁ ማለቱ ነው፡፡ እውነታው ድንበር ተጥሷል፤ የጉግል ካርታ ግን ይህንን እውነታ ይቃረናል፡፡

ተጨማሪ ከፈለግህ…፣ የአማራን ክልል ካርታ ከ google ፈልግ! ፈለግህ? ለየት ያለ ካርታ አገኘህ?… ድርቅ/ክው ብለህ ቀረህ? እኔን ድርቅ/ክው ያድርገኝ!

አየህ..የጨዋታው ጌም ውርርድ የሚካሄደው በክልልና አገር ምስቅልቅል ካርታ /scribble map/ መሆኑ ጨዋታውን ለየት ያደርገዋል፡፡ የሚገርምህ የክልልና አገር ካርታ ጨዋታውን ለማሸነፍ የሚመዘዘው የማሸነፊያ ካርድ “ጆከር” ጉግል ሰርች ላይ ይፈለግልን መባሉ ነው፡፡ ይህ የ google ምስክርነት ደግሞ ነገ…ከነገ ወዲያ ከወንድሞችህ ጋር ጦር እንዳያማዝዝህ፣ ሰሞኑን ያየኸውን የ EBC የኢትዮጵያን አይነት ካርታን መቃወምህ አርቆ አስተዋይነትህን አሳይቶኛል፡፡ ይህ የካርታው ጨዋታ ከአሁኑ ይቀየር ማለትህ፣ በ google ዳኝነት ነገ የሚደረገውን “ጦርነት” አንተ አልፈልገውም እያልክ ነውና አንተ ልትመሰገን ይገባል፡፡

ሲጠቃለል…የነገን “ክፉ ነገር” ከፈራን አይቀር፣ የEBC ብቻ ይቅርታ ጥቅም የለውም፡፡ እንደ መረጃ በ google ላይ የተቀመጡት የተበላሹ የኢትዮጵያ ክልል ካርታዎች መወገድ የነገ የሰላም ዋስትናዎቻችን ሊሆኑን ይችላሉና የሚመለከታችሁ አካላት አስቡበት ለማለት ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *