ጥጋበኞችን ለመቆጠር በሚል በደሃው ስም በሚሊዮኞች ደግሞ ይበደራሉ፡፡

ቆይ እስቲ ብድሩን ማን ነው የሚከፍለው?
ሲሳይ በዛብህ
ባለፈው ሳምንት ታላቋ ራሽያ ቀደም ሲል የቀድመዋ ሶቬይት ህብረት ተበድራው የነበረውን ብድር ከፍላ ጨረሰች የሚል ዜና በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲነገር ነበር፡፡ ምዕራብያኖች መቼም አያልፉም፡፡ ይሄን ዜና ላነበበ ኢትዮጵያዊ የአገሩ ሁኔታ የማያስጨንቀው የለም ፡፡ ለምን ቢባል 30 ቢሊዮን የደረሰው ብድር ማን ነው ሚከፍለው? የወያኔን ዱርየ መንግስት ግን አይጨንቀውም፡፡ እንዴውም ብድሩ እንዴት ለመፃይቷ ትግራይ ለምትባል ትንጥየ አገር እንደሚውል ማለም ከጀመሩ ይሔው 26 አመት ሆናቸው፡፡ ህልማቸውንም እውን ለማድረግ በአንድ ግለሰብ ላይ ተንጠላጥለው ነበር፡፡ እሱም ወደ ሲኦል ሲሄድ- ይሄው የእውር ድንግር በመሄድ ላይ ናቸው፡፡ መቼና እንዴት አዲስቷን ትግራይን ለሚዘርፉት ህዝብ ማብሰር እዳለባቸው እንኳን ሳያውቁ ሊበታቱኗት ያሰቧትን ኢትዮጵያ ካርታዋን በቴሌቨዥን መስኮት አሳይተው በፌስቡክ አካንታቸው ደግሞ ተሳስተን ነው የሚል የጅል-ይቅርታ መጠየቅ ጀምረዋል፡፡ ጊዜ ይስጠን እንጂ ብዙ እናያለን! ሆኖም እቺን ቅድሰት አገር በድሎ በሰላም የኖረ ግን በታሪክ መዝገብ ላይ እንደሌለ ሊያውቁት ይገባል፡፡
የዚህን ሳምንት ሪፖርተር ‹‹ በአዲስ አበባ አዲስ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ በመስከረም ስራ ላይ ሊውል ነው›› ይላል፡፡ ሪፖርተር የተጠቀመበት ፎቶ በራሱ ከተማዋ መቼ እንደልብ የሚያንከላውስ መንገድ አላትና ነው ፍጥነት መቆጣጠሪያ ያስፈለጋት ለማለት በቂ ነው፡፡ የብድር ገንዘብ በእንደዚህ አይነት እንተፈንቶ እንዲወጣ የሚደረገው ከህዝብ ክትትል ውጭ ስለሆነና ለዝርፊያ ቀላል ስለሆነ ነው፡፡ አለም ባንክም ወደ 82 ሚለዮን ዶላር ለእንደዚህ አይነት ውንብድና ሊያበድር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚገርመው የአገሪቷ ነባራዊ ሁኔታ ለማይፈቅደው ለሶፈትዌር ግዢ በሚል በሚሊየኖች በሚቆጠር ገንዘብ ከጎረቤት አገር ኬንያ እየሄዱ መግዛት የተለመደ ነው፡፡ ለምን ቢባል የኢንተርናሽናል ጨረታ ጨዋታ ስለሚያሟላ! ባንኩም ያበድራል፡፡ ለምሳሌ የአዲስ አበባ የመሬት ማኔጅመንት ለማቀላጠፍ በሚል በብድር የተገዛው ሶፍት ዌር ማን ጋር እንዳለ እንኳን አይታወቅም ግን ብዙ ሚሊየን ዶላር የብድር ገንዘብ ወጥቶበታል፡፡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮም አንዱ ነው፡፡ ለሶፍትዌር ግዢ በሃያ ሚሊዮን የሚቆጠር ወጪ ያወጣል፡፡ መጨረሻም የSoftware CDውን መሳቢያ ዉስጥ ቆልፈው ይጠፋሉ፡፡
እና ዱሪየው ወያኔ ሊዘርፍ ሲፈልግ መጀመሪያ በሪፖርተር ያስነግርና ህዝቡ ተገርሞ ዝም ይላል የሚል የወረደ የወንበዴ ስሌት አለው፡፡ ለምሳሌ ጋዜጣው ጠጥቶ ማሽከርከርን ለመቆጠጠር የሚረዳው መሳሪያ ስራ ላይ ሊውል ነው ብሎ እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ የትንፋሽ መመርመሪያውን ገዙ፡፡አንዱን ብቻ በ250 ሺህ ብር ሂሳብ ፡፡ የሚገርመው ግን የተገዛው መሳሪያ የያዘው የባለስልጣን ልጆች እና ገንዘብ የሚጥሉበት ቦታ ያጡ ሃብታሞችን ነው፡፡ ጠጥቶ -ማሽከርከር የ99.99% የከተማዋ ነዋሪ ችግር አይደለም፡፡ ደሃው መች ደላውና፡፡ እንከኳንስ ሊጠጣበት ቁርስ-ምሳ-እራቱንም በሺፍት ነው የሚበላው፡፡ ለከተማዋ የትራፊክ አደጋ ምንም በሚያስብል ደረጃ ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም፡፡ እነዚህ ጥጋበኞች አደጋ ቢያስከትሉ አንኳን አንድ ቀን አይታሰሩም፡፡ ቀድሞውንም ጥጋበና ስለሆኑ በቅጣትም አይመለሱም ምክንያቱም ጥጋባቸው ከስርአቱ የመነጨ ስለሆነ፡፡ ሲፈልጉ ትራፊኮቹን ያሳስራሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህን ጥጋበኞችን ለመቆጠር በሚል በደሃው ስም በሚሊዮኞች ደግሞ ይበደራሉ፡፡ የከተማዋን የተቃጠለውን የመንገድ መብራት አምፖል እንኳን ቢቀይሩ ስንት ለውጥ በመጣ፡፡ በአጠቃላይ ለህዝቡ የተረፈው የማደናገሪያው እንግሊኛ ቋንቋው ነው-speed control camera, alchol tester, ወዘተ፡፡ ነገር ግን- ደሃው መንዳት በማይችሉ ሲኖ-ትራክ አሽከርካሪዎች መሞቱ ቀጥሏል!!
በመቀጠልም በዚህ የወያኔ ድምፅ-ሪፖርተር ‹‹ሞተር አልባ ተሽከርካሪዎችን አገልግሎት ለማስፋፋት የሚያስችል አዲስ ስትራቴጂ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ አስታውቋል›› ፡፡ የሚገርመው መስተዳደሩ ህዝቡን መናቁን የሚያሳየው በኢቢሲ እንኳን የተተቸውን የኤምፔራል መንገድ ላይ ለፈሰሰው 16 ሚልዮን የብስኪሌት ግዢ ተጠያቂ ሳይኖር ተጨማሪ ከአለም ባንክ በ170 ሚሊዮን ብድር ዝርፊያውን ለሚከናወንበት ስትራቴጂ ያወጣል፡፡ በጣም ይገርማል!
እንደመዝጊያ ባለፈው ቆራጡ ጠ/ ሚኒስቴራችን የመንግሰት ቢሮዎች ወጪ እንዲቀንሱ አስገነዘበና አሳቀኝ፡፡ ለምን ቢባል የሱ ሰዎች የሚባሉት ሁሉ (ወንድሙም አቶ ገነቱ ደሳለኝ ጭምር) ስልጣንና ገንዘብ ያገኙት አዳዲስ በተመሰረቱ መ/ቤቶች የቤት ክራይ፣ የመኪና ግዢ፤ የቢሮ ዕቃዎች ግዢ መሆኑን ረስተውት መሆን አለበት፡፡ በከፊል ልጥቀስ ከተባለ – የውሃ ስራዎችና ቁጥጥር ፤ የመንግስት መ/ቤቶች ግንባታ ቢሮ…፡፡ እናም የከንቲባ ደሪባ ትራንስፖርት ቢሮም ሆን ብሎ በሰላም አንድ የነበረውን ቢሮ ወደ አራት የተለያዩ ቢሮዎች ኤጀንሲ፡ባለስልጣን፤ ፈንድ ፅ/ቤት እያለ ከፋፈለው፡፡ ከፋፍሎም አዳዲስ ዘመድ መግዢያ ሹመኞችን ሾመት፡፡ ዝረፊያውም መንግስታዊ ሽፋን ተሰጠው፡፡ ከዚያማ ዝርፊያውን በቤት ክራይ፣ መኪና..ወዘተ እያለ አጧጧፈው፡፡ በካሬ ሜትር 450 ብር ለሚከፈልበት ህንፃ የተረፋቸውን ቦታ ሁሉ በተሰባበሩና በሚጣሉ ወንበሮች ሞሉበት፡፡ ከ 1.7 ቢሊዮን በጀቱ አብዛኛውን ለቢሮ ማቋቋሚያና ነው የዋለው፡፡ በዚህም የስራ ሃላፊዎቹ ከያሪስ እስከ ፕራዶ፤ከአባዱላ እስከ ኒሳን እያማረጡ ሲንፈላሰሱ በክረምት ዝናብ እየመታው ታክሲ የሚጠብቀውን ህዝብ ሲያዩ ምንም ሃፍረት አይሰማቸውም፡፡ እንዲያውም የዝናብ ውሃ እየረጩ ቢዝነሳቸውን ለማጧጧፍ ወደ ቀድሞ ኤምፔራል ሆቴል(አሁን ሜቴክ በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ሆቴል) ይበራሉ፡፡
የሚገርመው ግን እያንዳንዱ ምን እንደሚያደርግ ህዝቡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ዝርዝር መረጃ አለው፡፡ እንደ ደርግ ጊዜ ህዝቡ የዋህ አየደለም፡፡ ያኔ ህዝቡ መረጃ በለመያዙ አብዛኛዎቹ የደርግ ባለስልጣን የእጃቸውን አላገኙም፡፡ አሁን ግን ከንቲባውን ደሪባ ኩማን ጨምሮ የሜቴክ ምድበተኛውና የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ይሄን አገሪቷ የምትበደረው ለ300 ሚ ዶላር ብድር አጠቃቀም ተጠያቂዎች እነደሆኑ ሊያውቁት ይገባል፡፡ አለበለዚያ ግን በእርግጠኝነት ሂሳቡን እስከነ ልጆቻቸው እንደሚከፍሏት ነው፡፡ ያኔ ተፀፅቻለሁ መልስ አይሆንም -ለነሱም ለኛም፡፡ ምክንያቱም ጉዳት ደርሷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *