የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የጉዞ ማስጠንቀቂያ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የጉዞ ማስጠንቀቂያ
#Ethiopia #USState.gov #Amhara #Oromia #VOAAmharic
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውስጥ የተቃውሞ እንቅስቃሴና በስፋት የማሰር ተግባር ሊኖር ይችላል በሚል ለአሜሪካ ዜጎች የጉዞ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል። በተለይም በአማራ ክልል በጎንደርና በባህርዳር እንዲሁም በአንዳንድ ኦሮሚያ አከባቢዎች ተቃውሞ መኖሩን የሚጠቁሙ ዜናዎች በመኖራቸው ዜጎቹ እንዲጠነቀቁ አሳስቧል። “አዲሱ ማስጠንቀቂያ ባለፈው ሰኔ ወር ወጥቶ የነበረውን ይተካል” ይላል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ።
የኢትዮጵያ መንግሥት ድረ-ገጾችን፣ ተንቀሳቃሽ ስልክንና የስልክ መስመርን የመገደብ ወይም የመዝጋት ዝንባሌ አለው ያለው ማስጠንቀቂያው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ከአሜሪካ ዜጎች ጋር የመገናኘት ብቃቱን የኢትዮጵያ መንግስት ይገድባ፣የአሜሪካ ኤምባሴ ለዜጎቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ይገድባል። የአሜሪካ ዜጎች ቢታሰሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ለአሜሪካ ኤምባሲ አያሳውቅም ይላል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ያወጣው መግለጫ።
ኢትዮጵያ ያሉት የአሜሪካ ዜጎች ከኤምባሲ ጋር የሚገናኙበት አማራጭ መንገድ ሊኖራቸው ይባድባል። የአሜሪካ ዜጎች የተንቀሳቃስ ስልካችውን ቁጥር በኤምባሲው ማስመዝገብ አለባቸው። Smart Traveler Enrollment Program በተባለውም መመዝገብ አላባቸው ሲል የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጥብቆ ይመክራል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *