አንበሳ ሲራመድ ቀስ እያለ ግራና ቀኙን እያየ ስለሚጓዝ ኮቴው አይሰማም

#ETHIOPIA | አንበሳ ሲራመድ ቀስ እያለ ግራና ቀኙን እያየ ስለሚጓዝ ኮቴው አይሰማም። ሲራመድም ለእይታ በማያጋልጠው መልኩ ተጠንቅቆ ስለሚራመድ አንበሳ ወደነሱ እየመጣ መሆኑን ሌሎች የዱር እንስሶች በቀላሉ አይረዱትም። አንበሳ ወደ እነሱ እየመጣ መሆኑን ከሁሉም ቀድሞ በሩቁ የሚያዩት በዛፍ ላይ ያሉ እንደ ጦጣ ዝንጀሮና ጉሬዛ የመሳሰሉት ናቸው። ሌሎች በምድር ላይ የሚኖሩ እንደ ከርከሮ ፣ አሳማ ፣ ድኩላና አጋዘን የመሳሰሉ የዱር እንስሳቶች ግን በዛፍ ላይ የሚኖሩ እንስሳቶች አንበሳውን በሩቁ አይቶ በድንጋጤ ከዛፍ ዛፍ እየዘለሉ በመጮኽ አከባቢውን ሲረብሹ እየሰሙ እንኳን አንበሳው ወደነሱ እየመጣ መሆኑን አይረዱትም።
እነዚህ በምድር ላይ የሚኖሩ የዱር እንስሳቶች አንበሳ መምጣቱን የሚረዱት ድንገት ከተፍ ብሎ አጠገባቸው ቆሞ ሲያዩት ብቻ ነው።

እና ምን ለማለት ነው ሰውዬው እየመጣ መሆኑ ያልታየው ለእኛ ነው እንጂ ዛፍ ላይ (ስልጣን ላይ) ያሉት ሕወሓቶች ሰውዬው ገስግሶ እየመጣ መሆኑን ከሩቁ አይቶ በድንጋጤ መንጫጫትና መረበሽ ከጀመሩ ቆይቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *