አማራን ሸንሽነው ታላቋ ትግራይን ሲገነቡ የአማራ ልጆች የት አላችሁ?

ቅማንት-አማራ፣ ህወሃት እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ
Damtew Neftegna

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህር ሆኘ ስቀጠር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር (ያኔ ዶክተር) መንገሻ አድማሱ ነበሩ። ፕሮፌሰር መንገሻ፣ መንጌ ልክ እንደ መንጌ (መንግስቱ ሃ/ማርያም) ኮስተር ያሉ ነበሩ! የደቡብ ጎንደር ተወላጅ ናቸው። ያው እንደማንኛዉም ሰው ብዙ ደጋፊ ብዙ ተቃዋሚም ነበራቸው። ለዩኒቨርሲቲዉም ይሁን ለጎንደር ማህበረሰብ ቀላል የማይባል አስተዋጾ አበርክተዋል።

የእሳቸው ምክትል (አካዳሚክ) ፕሮፌሰር ተፈራ ነበሩ። ተፌ በጣም የተከበሩ የፋርማሲ ባለሙያ ናቸው። እሳቸው ያስተማሯቸው ተማሪወች ስለ እሳቸው ጎብዝና እና የማስተማር ችሎታ አዉርተው አይጠግቡም። እኔም በተደጋጋሚ ከእሳቸው ጋር ለመወያየት እድሉ ነበረኝ፣ በጨዋታ እያዋዙ ቁም ነገር ሲያስተምሩ ግሩም ሰው ናቸው። ነገር ግን ይህንን ክብራቸዉን በስልጣን ዘመናቸው ማስቀጠል አልቻሉም። ብዙ ነገር ተወራባቸው፣ መምህራኑ ሁሉ አማረሩ እና እንድወርዱ ተደረገ…. ስለማከብራቸው ብቻ ሳይሆን የዚህ ጽሁፍ አላማም ስላልሆነ ወደ ዝርዝሩ አልገባም።

በዚህ አጋጣሚ ነበር ዶክተር ደሳለኝ መንገሻ የም/ፕሬዝዳንትነት ስልጣኑን የያዙት። ዶ/ር ደሳለኝ የእንሣት ህክምና ባለሙያ ናቸው። በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ቀርቤ እንዳየኋቸው ጥሩ ሰው ከመምህራን ጋር በቅርበት የሚወያዩ ነበሩ። አሁን ጥቃቄዉ ከዩኒቨርሲቲዉ መማር ማስተማር ዉጭ ያላቸው ሚና እና እንደት በፍጥነት ፕሬዝዳንት ሆኑ የሚለው ነው?

እዚጋ ልብ በሉ የዚህ ጽሁፍ አላማ ቅማንት እና አማራ እያሉ መከፋፈል አይደለም! እዉነታው መነገር ስላለበት ነው። ለእኔ ሁለቱም አንድ ናቸው። ከፕ/ር መንገሻ በፊት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ግዛው (የህብረተሰብ ጤና ባለሙያ) ነበሩ። ፕ/ር ግዛው ቅማንት ስለሆኑ ወያኔ አማራን ለመከፋፈል ሊጠቀምባቸው ፈልጎ ነበር። ነገር ግን ፕ/ር ግዛው ባሳዩት እምቢተኝነት ከፍተኛ ጫና ስለደረሰባቸው ስልጣናቸዉን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ። በዚህም በአንዳንድ የወያኔ –ተላላኪወች ጥርስ ተነክሶባቸዋል።

የፕ/ር ግዛው እቅድ የከሸፈበት ህወሃት አንዳንድ ጥቅመኛ ቅማንት-አማራወችን መጠቀም አቀደ። ም/ል ፕሬዝዳንቱን (ፋይናንስ) ጨምሮ በየቦታው የተሰገሰጉትን የትግራይ ተወላጆች እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለዚህ እቅድ ግንባር ቀደም ተዋናይ ዶ/ር ሲሳይ ይፍሩ (የህክምና ሳይንስ ኮሌጂ ድን) ናቸው። የተለያዩ ፋካልቲ ድኖች በየሁለት እና ሶስት አመት ሲቀያየሩ በጣም ብዙ ምሁራኖች እና የህክምና ዶክተሮች ያሉት የጎንደር ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ድን ዶ/ር ሲሳይ ግን ነኪ በማጣታቸው ስልጣን ከያዙ በቅርቡ ድፍን 10 አመት ይሞላቸዋል። በዩኒቨርሲቲው የህወሃትን አጀንዳ እንደወረደ በማስፈጸም ይታወቃሉ። ዶ/ር ሲሳይ ጎንደር አዉቶፓርኩ የሚገኘው እና በህወሃቶች የተቋቋመው የቅማንት የማንነት ጥያቄ ም/ፕሬዝዳንት ናቸው።

እዚህ ላይ የህወሃትን እባብነት ተመልከቱ። በወቅቱ በተካሄደው ህዝብ እና ቤት ቆጠራ የቅማንት ህዝብን ቁጥር ዜሮ አደረጉት። ይህ ስትራቴጂ የአማራን ቁጥር መቀነስ አንዱ አካል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ይህም በተለይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ከፍተኛ ቁጣን አስነሳ። ነገሩን ለማብረድ ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሰማያት ስብሰባ ጠሩን። በዚህ ስብሰባ ፕ/ሮ ይግዛው ከምርጫ 97 እስከ አማራ ህዝብ ቁጥር መቀነስ በጭብጨባ የታጀበ አስገራሚ ንግግር አደረጉ። ወያኔ ግን አፍ እንጂ ጆሮ የለዉም እና ዶ/ር ስንታየሁ በህወሃት የተሞላዉን ፕሮፓጋንዳ አራግፎብን ሄደ። ፕ/ር ይግዛዉም የህወሃትን ተንኮል ዘነጉት መሰል የቅማንት ህዝብ የማንነት ጥያቄን ተቀላቀሉ፣ በግዜዉ የቅማንት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ሊቀመንበር ሆኑ። አሁን ህወሃት እቅዱ ተሳካለት። ፕ/ር ግዛዉን ወጥመድ ዉስጥ ጣሏቸው።

ፕ/ር አድማሱ ይህንን የህወሃት ሴራ ስለሚያቅ በተደጋጋሚ ከዶ/ር ሲሳይ ጋር ይጋጩ ነበር። በመጨረሻም የህወሃት ሴራ አሸነፈ እና ፕ/ር አድማሱን አዉርደው በሚገርም ፍጥነት ዶ/ር ደሳለኝን ፕሬዝዳንት አደረጉት። አሁን ከፕሬዝዳንት እስከ ድፓርትመንት ሁሉም በህወሃት እና አንዳንድ ተላላኪ ቅማንቶች ተሞልቷል። በፕ/ር መንገሻ እና በፕ/ር አፈወርቅ (ያኔ የምርምር ም/ፕሬዝዳንት አሁን ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴታ) አመራር በሃገር አቀፍ ደረጃ 1ኛ እና 2ኛ ሲወጣ የነበረው ዩኒቨርሲቲ አሁን እንደሌሎቹ ዩኒቨርሲቲወች ሁሉ የካድሬ መፈልፈያ ማሽን ሆነ።

ዛሬ ጎንደር ዩኒቨርሲቲን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ያደረገው ህወሃት እነዚህን ጥቅመኛ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በመጠቀም አማራን የመከፋፈል አጀንዳቸዉን ተያይዘዉታል። የነ ዶ/ር ሲሳይን የቅማንት ለምድ ለብሰው ቅማንት ቅብርጥስ እያሉ ጎንደርን ወደ 3 የመከፋፈል አጀንዳቸዉን ይፋ አድርገዋል። ህወሃት የወልቃይትን እና የራያን ጥያቄ ለ25አመት ሳይመልስ ቅማንት የሚል ጥያቄ እራሱ ጠይቆ እራሱ ካልመለስኩ እያለ ነው። ይህ አማራን የመከፋፈል አጀንዳ በወሎ ተጀምሮ ጎንደር ደርሷል። የጎጃም አገው የሚለዉ ቀጣይ አጀንዳቸዉንም በሰፊው እየሰሩበት ነው።

አማራን ሸንሽነው ታላቋ ትግራይን ሲገነቡ የአማራ ልጆች የት አላችሁ? ግፉ እና በደሉ የት ሲደርስ ነው በዓንድነት የምንንነሳው? እስከ አድዋ ድረስ ሂደው መስዋት የሆኑት አባቶቻችንስ ምን ይሉን? አንዳንድ የዋህ የቅማንት አማራወችስ እንደት ይህንን ተንኮል መረዳት አቃታችሁ? በተለይም የቅማንት ማንነት በሚል ሽፋን የህወሃትን አጀንዳ ለማስፈጸም መጸሃፍ እየጻፋችሁ ያላችሁ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ብታስቡበት ይሻላል። እዉን ህወሃት መቀሌ ላይ ቢሮ የከፈተላችሁ ለእናንተ አስቦ ይመስላችኋልን? ህወሃቶችስ የዚህ ሁሉ ግፍ እና በደላችሁ አጸፋ ሊከፋ እንደሚችል እንደት መረዳት አቃታችሁ?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *