የህወሓት ወታደሮች ስርዓቱን በመክዳት የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይሎችን እየተቀላቀሉ ነው።

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
*************************************
የህወሓት ወታደሮች ስርዓቱን በመክዳት የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይሎችን እየተቀላቀሉ ነው።
—————————————————————————————————–
በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ከተማ ከሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ በነሀሴ ወር 2009 ዓ/ም ቁጥራቸው ከ 11 በላይ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ስርዓቱን በመክዳት በአካባቢው ወደ ሚገኙት የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬች ጋር ተቀላቅለዋል ፣ ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ በከተማው በሰዎች ላይ በደልን እና ድብደባን ሲፈፅም በነበረ የህወሓት ወታደር ላይ የከተማ ውስጥ ታጋዬች ጥቃት በመፈፀም በወታደሩ ላይ ጉዳት አድርሰው ይዞት የነበረውን ሙሉ ትጥቅ በመቀማት ወደ ታጋዬች ተቀላቅለዋል። የስርዓቱ ወታደሮች በክህደትና ጥቃት ተፈፅሞበት ትጥቁን በተቀማው ወታደር ምክንያት የከተማውን ህዝብ በማንገላታት ላይ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ባለሆቴሎችና ባለመጠጥ ቤቶች እየታሰሩና እየተንገላቱ ይገኛሉ፣ የአካባቢው ህብረተሰብ እያመረረ እና ስርዓቱን በኃይል ሳይቀር እየታገለ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *