ህወሃት የሶሻል ሚድያ ካድሬ ግብረ-ሃይል

ህወሃት የሶሻል ሚድያ ካድሬ ግብረ-ሃይል

Internet troll

ህወሃት ፌስቡክ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ እያደረገ ያለውን የነጻነት ትግል የሚያዳክሙ የሶሻል ሚድያ ካድሬ ግብረ-ሃይል ማሰማራቱ ይታወቃል። በመቀሌ እና አዲስ አበባ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኮምፒውተሮች ፊት ለፊት የህወሃት የካድሬ ግብረ-ሃይል አባላት በየቀኑ ተቀምጠው ይገኛሉ። (የካድሬ ግብረ-ሃይል አባላቶቹ በርካታ የፌስቡክ አካውንቶች ሲኖሯቸው የአብዛኛዎቹ አይ ፒ አድራሻ ‘IP Address’ ተመሳሳይ ነው። ይህም ማለት የህወሃት ካድሬ ግብረ-ሃይል አባላት በአንድ ቦታ ተሰብስበው ስራቸውን ያከናውናሉ ማለት ነው)።

የህወሃት ሶሻል ሚድያ ካድሬ ግብረ-ሃይል የነጻነት ሃይሎች እያደረጉ ያሉትን ተጋድሎ፣ ህዝባዊ አድማዎችና ህዝባዊ እምቢተኝነቶች በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንዳይሰሙና አንድ ወጥ የሆነ መልክ እንዳይዙ ከኢትዮጵያ የሚወጡ ዘገባዎችን “የሀሰት ናቸው” እያሉ ኮሜንት (አስተያየት) መስጠት ከበርካታ ተጋብሮቻቸው ውስጥ ዋንኛው ነው።

ይሁንና አልፎ አልፎ ስህተት መስራታቸው አልቀረም ለምሳሌ “ተስፋሁን” የተባለው ካድሬ መቀሌ ካለው የካድሬ ግብረ-ሃይል ጣብያ ተቀምጦ “ሀዋሳ ላይ አድማ እየተደረገ ነው” በሚለው ዘገባ ስር “እኔ እዛው ነበርኩ ምንም ነገር የለም” በማለት ኮሜንት ይሰጣል… ትንሽ ቆየት ብሎ ደግሞ “ባህርዳር የቦንብ ፍንዳታ ተፈጸመ” በሚለው ዘገባ ስር “እኔ እዛው ነበርኩ ውሸት ነው” በማለት አስተያየት ይሰጣል። እንግዲህ ካድሬ ተስፋሁን በብርሃን ፍጥነት የሚጓዝ ካልሆነ በስተቀር በጥቂት ሰዓታት ልዩነት ባህርዳር እና አዋሳ ሊገኝ አይችልም።

በተደጋጋሚ የህወሃት ሶሻል ሚድያ ካድሬ ግብረ-ሃይል አባላት “ዜናው ውሸት ነው፣ እዚያው ነበርኩ” በሚሉበት ወቅት የህወሃት የክልል ኮሚኒኬሽን መስራቤቶች ሁኔታው እንደተፈጸመ በራሳቸው ቋንቋ ይገልጻሉ።

በእንደዚህ አይነቱ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች በእንግሊዘኛው ትሮልስ (Trolls) እየተባሉ የሚጠሩ ሲሆን የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም በጣም አስቀያሚ ፍጥሩ ጉድጓድ ውስጥ ተሸሽጎ የሚኖር እንደማለት ነው።

በነገራችን ላይ ይህ ተግባር በአምባገነን አገዛዞች የተለመደ ነው ለምሳሌ ቻይና እና በርካታ የአረብ ሀገራት ከሰው ሃይል በተጨማሪ ቦት ፋርም (Bot farm or Click Farm) ሶፍትዌሮች ይጠቀማሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *