ሰበር ዜና) በሰሜን ጎንደር ዞን፣

(ሰበር ዜና)
በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ጭልጋ ወረዳ፣ ነጋዴ ባህር ከተማ የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች አድማ የመቱ ነጋዴዎችን ማሰር እና መደብደብ መጀመራቸውን ተከትሎ ሌሊቱን የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ወደ ከተማዋ ዘልቀው በመግባት ከወታደሮቹ ጋር ተኩስ መግጠማቸውን ታማኝ ምንጮች አሳውቀዋል።
በውጊያው ቢያንስ 3 የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች እንደተገደሉ እና 4 ያህል ደግሞ እንደቆሰሉ ታውቋል ያሉት ምንጮች ተኩሱ ለ45 ደቂቃ ያህል የቆየ እንደመሆኑ የጉዳቱ መጠን ሊጨምር ይችላል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *