በሀዋሳ ትላንት የተጀመረው የባጃጅ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሏል።

#ESAT
መረጃ ከሀዋሳ
በሀዋሳ ትላንት የተጀመረው የባጃጅ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሏል። በአስፓልት መንገዶች ላይ አገልግሎት እንዲያቆሙ በመደረጋቸው የተቃወሙት የባጃጅ አሽከርካሪዎች በትላንትናው ዕለት ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውንና የመንግስት ተሽከርካሪዎችን ማጥቃታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ዛሬ ጥያቄ ይዘው ወደሚመለከተው አካል ቢሄዱም ተቀባይነት አላገኙም። በአድማው ቀጥለዋል። በሌላ በኩል በሀዋሳ አዲሱ ገበያ ዛሬ ሌሊቱን ከ20 በላይ ሱቆች በግሬደር መፍረሳቸውን ተከትሎ በአከባቢው መለስተኛ ውጥረት መፈጠሩ ተገልጿል። ወደ ገበያው የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ እንደነበርና ሱቃቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ተቃውሞ እያሰሙ መሆኑንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *