የአርበኞች_ግንቦት_፯_የሰሜን_ኢትዮጵያ_ዕዝ ! ! ! በአማራ ክልል የ3 ቤሮ ኃላፊዎች ከፀጥታ ክፍሉ ጋር ግጭት ውስጥ ገቡ ።

#የአርበኞች_ግንቦት_፯_የሰሜን_ኢትዮጵያ_ዕዝ ! ! !
በአማራ ክልል የ3 ቤሮ ኃላፊዎች ከፀጥታ ክፍሉ ጋር ግጭት ውስጥ ገቡ ።
በ 2008 ዓ/ ም መጨረሻ ጀምሮ በተነሳው ህዝባዊ አመፅ ምክንያት የተለያዪ ቢሮዎች የስራ ተሽከርካሪዎችን ነዳጅ እና የሹፊር አበል እየቻሉ ለፀጥታ ኃይሎች እዲመድቡ በተላለፈው ጥብቅ መመሪያ መሰረት ሁሉም ቢሮዎች ማለት ይቻላል ሲያቀርቡ በመክረማቸው የ2009ዓ/ ም በጀት አፈፃፀም ሲገመገም አብዛኛው ለልማት የተባለው በጀት ሙሉ በሙሉ በፀጥታው በመበላቱ የያዝናቸውን የስራ እቅዶች እሩቡንም መተግበር አልቻልነም ፣በዚህ የተነሳ ለህዝባችን ቃል የገባነውን መስራት ባለመቻላችን ከህዝቡ ከፍተኛ ወቀሴታና እምነት አጥተን እንገኛለን የ2010 ዓ/ ም በጀትን በተመለከተም ከህዝብ ጋር የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ሞራል አጥተን መድረኮችን አላደረግንም ፣ በመሆኑም አሁንም ከፀጥታ ክፍሉ እየቀረበ ያለውን የተሽከርካሪ ፣የነዳጅና የሹፊር አበል ለመክፈል እጅግ የተቸገርን በመሆኑ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መፍትሄ ሊሰጥበት ይገባል ሲሉ የክልሉ ጤና ቢሮ ፣የክልሉ ግብርና ቢሮ እና የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የጠየቁ ሲሆን ይሄን ተከትሎ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገድ አዳርጋቸው ይሄን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ለውይይት የጠሯቸው የፀጥታ ክፍሎች እጅግ ስሜተኛ በመሆን ቁጣ በተቀላቀለበት እንቢተኝነታቸውን የገለፁ ሲሆን አክለውም ” እኛ እኮ አለን ሌት ከቀን ፀሀይና ብርድ ዝናብ እየተፈራረቀብን ሕይወታችንን አሳልፈን እየሰጠን እነሱ እንዴት ለመኪናና ለገንዘብ ይሳሳሉ ፣ደግሞስ በሙስና ገንዘቡን የሚጨማለቅበት ማነውና? የትኛውን ልማትስ ሰርተው ነው ? እንደዚህ የሚሉት ያውስ አንሱ በፈጠሩት የመልካም አስተዳደር ችግር አይደለም ወይ ይህ ሁሉ ጦስ የመጣብን? ወዘተ ” የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን አቶ ገዱም በቀጣይ ተወያይተን መፍቴሄ እስክናስቀምጥ በነበረበት ይቀጥል የሚል ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል። በመሆኑም የአገሪቱን ሃብት በሙስናና ህዝብን ለመጨቆን እያዋሉት መሆኑን በግልፅ ስንለው የነበረው ትክክል መሆኑን ያሳያል፣ በመሆኑም ያለፈው አልበቃቸው ብሎ አሁንም በዚህ መንገድ ለመቀጠል የወሰኑና እየሰሩበት እንደሚገኝ ህዝባችን እዲያውቅና በምንም መንገድ ግብርም ሆነ ሊሎች መዋጮዎችን ባለማድረግ የመጨረሻ ሞታቸውን ማፋጠን አለብን እያልን ለህዝባችን ጥሪያችንን እያቀረብን ከዚህ ዜና ጋር አብረን የላክነውን ፎቶ ስትመለከቱ ይበልጡን ከህዝባችን እና በህዝባችን ስም ከአለም አገራት በብድርና በልመና የሚመጣውን ገንዘብ ጤና ጥበቃ እያዋለው ያለው የህፃናትንና የኗቶችን ሞት ለመቀነስ ሳይሆን ለመግደል ነው ፣ይህ እውነታ ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎች እየተደረሀ መሆኑን መረጃዎች ደረሱን ሲሆን ለመረጃ ሰጭዎች ደህንነት ሲባል ደብዳቤዎችን ከመልቀቅ የተቆጠብን ሲሆን ጊዜው ሲፈቅድ ይፋ የምናወጣቸው መሆኑን እንገልፃለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *