ትውልዱ እንቢ ብሏል

ትውልዱ እንቢ ብሏል
————————–
በአዴት ከተማ እረፍት ላይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሰብስቦ እሰብካለው
ያለው የወያኔ ፖንቱ ብአዴንን አፈር ድሜ እስበልተው ልከውልናል።
☞ ወያኔ መምራት አይችልም ለምን ስልጣን አይለቅም?
☞ ኢትየጵያ እስከመቸ ነዉ ያለጠቅላይሚኒስተር የምትመራዉ?
☞ከወያኔ ሺህ ጊዜ ደርግ ይሻለናል
☞ ”ትግራይ እስክትለማ ሌላው ሀገር ይድማ” የሚባለው ለምንድን ነዉ?
☞ ወያኔ እንደሚለዉ ከሆነ ቧንቧ ስተከፍት ወተት ይወርዳል ግን ወተቱ ቀረቶ
ዉሀ የለዉም
☞ አዴት ላይ በደርግ ጊዜ የነበሩ ጀነሬተሮች ና ትራንስፎርመርምች እየተነቀሉ
ትግራይ የሚሄዱት ለምንድን ነዉ?
☞ የአማራ ክልል ህበረተሰብ ላይጠቀም ለምን ግብር ይከፍላል?
☞ ብአዴን የህወህት አሽከር ነዉ
☞ አንቀፅ 39ን ህዝቡ ካልፈለገዉ ለምን አይነሳም?
☞ የትግራይ ህዝብ ሊያስብበት ይገባል በኃላ ህወሃት አይደርስለትም
☞ ከ3000 አመት በላይ ታረክ እያለን ለምን የ25 አመት ታሪክ እንድንቀበል
እንገደዳለን?
☞ አሁን ያለዉ ለወጥ ጊዜዉ የፈጠረዉ እንጅ ኢሀዲግ ያመጣዉ አይደለንም
☞ ብአዴን ነዉ አኛን አሳልፎ የሚሰጠን
☞ ጉልበት ለሂትለርም አልሆነ በቅርቡ መዉረዳችሁ አይቀሬ ነዉ
☞ እኛ ሳንሆን ወያኔ ነዉ ተምህክተኛ
☞ ያለፉ መሪዎቻችንን አታንሱብን, ያመናል, ምክንያትም ከእናንተሰለሚሻሉ
☞ ትግራይ ዉስጥ ስራ አጥ የለም ለምን?
☞ የጢስ አባይ ኤሌትሪክ ሀይል ማመንጫ አማራ ክልልን አልፎ ለምን መቀሌ
ሄደ?
☞ ለምንድን ነዉ የአማራ ክልል መሬት ለሁሉም አየተቆረሰ የሚሰጥ?
☞ ትግራይ ኢንደስትሪ መር ኢኮኖሚ ስትከተል እኛ ለምን ግብርና መር ኢኮኖሚ
እንከተላለን
እነዚህና ሌሎች በርካታ ጥያቄወች የአዴት ከተማ ከንቲባና ካድሬዎች በተገኙበት
በተማሪዎች ተነስቷል። መኳንንት ልጃለም የሚባለው የከተማዉ ከንቲባ
ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲስበደበድ ዉሏል። እንደተለመደው
በመዋሸትና በማድበድበስ ሊያልፍ ሲሞክር በመጮህና እንዳይናገር
በመከልከል ሲየስጨንቁት ዉለዋል ። በመጨረሻ የከተማዉ ከንቲባ ተማሪዎቹን
እንዲቀመጡ እየነገሩ ፀረ ዲሞክራሲ እርምጃ ከመዉሰዳችን በፊት ተቀመጡ
ሲል ተደምጧል ። ሁከቱ ካበቃ በኃላ ከንቲባዉ በአሁን ወቅት ሁከትና ብጥብጥ
ይነሳል ብለዉ በመስጋታቸዉ ተማሪዋቹን በንቀት አርፈው እንዲቀመጡና ምንም
እንደማያመጡ ተናግረዋል።
እንዲህ አይነት ትውልድ ሲፈጠር ነው ለውጥ ቅርብ የሚሆነው!!

ከ ህሊና ዘቀበሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *