የደብረ ታቦር ከተማ ማኅበረሰብ ሰማዕታቶቻችን በማክበር የሥራ ቦታዎች ሁሉ ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡

ደብረ ታቦር ፀጥ እረጭ ብላ ውላለች!

የደብረ ታቦር ከተማ ማኅበረሰብ ሰማዕታቶቻችን በማክበር የሥራ ቦታዎች ሁሉ ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡ ከንግድ ባንክ ውጭ ሁሉም የመንግሥትና የግል ድርጅቶች በሞላ ተዘግተዋል፡፡ የአድማ በታኝ ፖሊሶች በከተማዋ በብቸኝነት እየፈነጩ እንደሆነም ሰምተናል፡፡
ሌላው ግን የንግድና ኢንዱስትሪ ተላላኪ ቅጥረኞች እየዞ የንግድ ተቋማትን እያሸጉ እንደሆነም አውቀናል፡፡ አስተባባሪ ወጣቶች እነማን እንደሚያሽጉና ማስጠንቀቂያውንም እንደሚሰጡ እየመዘገባችሁ እንድትይዙም አሳስበዋል፡፡
የደብረ ታቦር ወጣቶች ባለፈው ዓመት የነበሩ ደኅንነቶችን መንጥረው በደረጃ ማስቀመጣቸው ለብዙ ቦታዎች ትምህርት ሰጭ ነበር፡፡ አሁንም ይኼው ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ጠላትን ለመለየት ዓይነተኛ አጋጣሚ ነው፡፡.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *