ካድሬው ኪዳነ ደሞ በንዴት በላብ ተጠምቆ “የወልቃይት ማንነት ተመልሶ ያደረ ነው፤ ትግራይ ውስጥ እየኖርክ አማርኛ መዝፈን አትችልም

ወያኔ ፈደራሊዝም፣ ሕገ መንግሥት እና የቀለም ወያኔ የሚል ርእስ በመያዝ የወልቃይት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመሰብሰብ እየደሰኮረባቸው ይገኛል፡፡
በተለይም በአዲ ረመጥ እየተካሄደ በሚገኘው ኪዳነ ገብረኪዳን የተባለ ጋጥ ወጥ የወያኔ ካድሬ እየመራው በሚገኘው ስብስባ የወልቃይት ተማሪዎች ገና በመጀመሪያው እንደተለመደው ለሰብሳቢ ካድሬዎች አልቀመስ ብለዋል፡፡ ግልጽ በሆነ ቋንቋ አማራነት እያስተጋቡ ነው፡፡ በመጀመሪያም ተማሪዎቹ ስንጠይቃቹህ ምትመልሱን መልስ እናውቃለን ግን አቋማችን እንድታውቁ እና ስሜታችን መግለፅ ሰለምንፈልግ በማለት ብዙ አሰታያየት እና ጥያቄዎችና በግልጽ አቋማቸው እያንጸባረቁ ይገኛሉ፡፡ ከተነሱት አሰተያየቶች በጥቂቱ:-
1)ወልቃይት አማራ ነው፡፡
2)የወልቃይት ማንነት ጠያቂ ኮሜቴ የኛ ተወካይ እና አባቶቻችን እንጂ በፍፁም አሸባሪ አደሉም፡፡
3)ማንነት በደም እና በዘር የሚገኝ እንጂ በይሁንታ የሚሰጥ እንዳልሆነ፡፡
4) EBC የወልቃይ ጠገዴና በአጠቃላይ የጎንደር ህዝብ አሸባሪ እያለ ይገኛል አንድ ነገር በሉት!?
5) “ሀይለ ስላሴ እና ሌሎች የድሮ መሪዎች መጥፎ እና ፀረ ህዝብ ነበሩ” ትላላችሁ ታሪክ ጠንቅቀን እናውቃለን እኮ የተጣመመ ታሪክ አታቅርቡልን፡፡
6) ወያኔ ከደርግ የሚለየው ደርግ በግልፅ እና በቀን ይጨፈጭፋል እናንተ ደሞ በድብቅ ሌሊት ሲሆን እና ሌሎች ግብረ መልሶች በስብሰባው ተንጸባርቀዋል፡፡
በተማሪዎቹ ቀርበው በካድሬዎች መመለስ ካልቻሉ ጥያቄዎች ደሞ ጥቂቶቹ ለናሙና የሚከተሉት ናቸው:-

1) ለምን የወልቃይት አማራ ባህል እያጠፋቹ በፍጹም የማናውቀውን አሸንዳ ለማስፋፋት ትጥራላቹ?

2) በሰላም መኖር ከተፈለገና አገሪቱ እንድትለወጥ የምትፈልጉ ከሆነ የወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ ለምን አትመልሱም?

3) ለምን የምንወደውና የምንሞትለት፣ የማንነታችን መግለጫ የሆነው አማርኛ ሙዚቃ ማድመጥ እና ማዘፈን ተከለከልን?

4)በዚህ ዘመን የወልቃይት ህዝብ እንደ ለምን ሌሎች ህዝቦች እኩል አይታይም (አማራ በመሆናችን እንደምትጠሉን እናውቃለን)?

5)ለምን ታፔላዎች(posters) ከአማርኛ ወደ ትግርኛ ይቀየራሉ?

እና ሌሎች ብዙ ጥያቄዎቸች ተነስተዋል ካድሬው ኪዳነ ደሞ በንዴት በላብ ተጠምቆ “የወልቃይት ማንነት ተመልሶ ያደረ ነው፤ ትግራይ ውስጥ እየኖርክ አማርኛ መዝፈን አትችልም፣ የታሰሩት አሸባሪዎች ሰለሆኑ ነው፣ እናንተ ታሪክ አታውቁም እና ሌሎች” አስቂኝ መልሶች መልሷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *