ይህን ሙሰኛ ዛሬም ዘራፋ ላይ ነው አንተነህ አብርሃም ማን ነው?

ስም አጥፊው አቶ አንተነህ አብርሃም ማን ነው?

ለምንስ በእንድህ አይነት ዘመቻ ግንባር ቀደም ሆነ?

አቶ አንተነህ አብርሃም በፌዴራሉ ፓርላማ በሚንስቴር ዲኤታ መዓረግ የመንግስት ተጠሪ ሆኖ የሚያገለግለዉን የአቶ አማኑኤል አብርሃም ወንድም ነው። የቀዳሚ እመቤት ሮማን ተስፋየና በርቀትም ቢሆን የ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ዘመድ የሆነው አንተነህ አብርሃም ከአንድ አመት በፊት እዚህው ኢትዮጵያ ዉስጥ በጋዜጠኝነት ሙያ ተሰማርቶ “የግንቦት ሃያ ፍሬዎች” የሚል የመንግስትን በጎ ስራዎች የሚያወድስ መፅሄት አዘጋጅ ነበር። ለከፍተኛ የደቡብ ባለስልጣናት ካለው ቅርበት የተነሳ ለግንቦት ሃያ የሚሆኑ ባነሮች፣ ቲሸርቶችና ኮፊያዎች በ አምስት ሚልየን ጨረታ ወስዶ ባቛራጭ የብዙ ሃብት ባለቤት የሆነ ሰዉ ነው።

እዚህ እያለ ለቅርብ ወዳጆቹ እንዲሁም በስልጣን ላሉት ዘመዶቹ የኣማራና የትግራይ ኢትዮጵያን የመምራት ጉዞ መገታት አለበት ብሎ በግላጭ ይናገር የነበረ ሰው ሲሆን አቶ መለስ እንዳረፉና አቶ ሃይለማርያም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው በተሾሙ ሰሞን ደግሞ “ወይዘሮ አዜብ መስፍን ቤተመንግስቱን አልለቅም አሉ” የሚል የሰም ማጥፋት ፁሁፍ በሰንደቅና በኢትዮሚድያ በማሰራጨት የመጀመርያ ግላጭ ዘመቻዉን ጀመረ። አንተነህ ይህ ሂደት የሰሜን የፖለቲካ የበላይነት መግቻ የመጀመርያ ርችት አድርጎ ይቆጥረው ነበር።

ወይዘሮ አዜብ ልቀቁ ሳይባሉ እንዲሁም ተለዋጭ ቤት ሳይሰጣቸው እንዴት ዉሽት ታትማላቹህ ተብሎ የሰንደቁ ዋና አዘጋጅ ሲጠየቅ ፁሁፉ ያመጣው አቶ አንተነህ አብራሃም እንደሆነና “የተወሰኑ ሰዎችም” ተፅእኖ እንዳረጉበት ተናገረ። በዚህ ሊከሰስ ዝግጅት ሲደረግ አሁንም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ኮሚሽነር አቶ አብዩ አልዩ ጣልቃ ገብተው ነገሩን ያስቀሩታል። ኮሚሽነሩ የአንተነህ ወዳጅም የቅርብም ሰው ናቸው።

“የደቡብ ፀሃይ ወጥታለች፣ እድሉን እንዳናጣው” ብሎ ሌት ተቀን የሚንገበገበው አንተነህና የዉስጥ አርበኛ ወዳጆቹ ከ ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ያገኘውን ያልተገባ ጥቅም ሊያሳስረው ስለሚችል አምና ወደ ዉጭ እንዲሄድ ያመቻቹና የዘረፈው ይዞ እልም አለ። ህወሓትን ለመገዝገዝ መለስን ማጠልሸት፣ መለስ ስለሞተ ደግሞ በሚስቱ በኩል መለስን በዜሮ ማባዛት በሚል ስሌት ላለፉት አራት አመታት ወይዘሮ አዜብ ላይ ዘምቷል። ለኢሳቶችም የፈጠራ ወሬ በመቀለብ ይንቀሳቀሳል።

አሁን ደግሞ የተለመደው መንገድ ላይ አቶ አባይ ፀሃየን ጨምሮ የህወሓት አምዶችን ለመገዝገዝ በተለያየ አካዉንቶች በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። እስካሁን ወደ ስምንት አካዉንቶች ያንቀሳቅሳል፣ አገር ዉስጥ ላሉ ፀረ ትግራይ ሃይሎችም ዉሸቱን እዉነት እያደረገ ይቀልባቸዋል፣ ይህን መስማት የሚፈልጉ ዘረኞች ደግሞ የትግራይ ግንዶች ባልዋቸው ላይ ይዘምታሉ።

አቶ አንተነህ አብርሃም የሚያራምደው “ሰዓቱ የደቡቡ ነው፣ አጋጣሚው እንዳያመልጠን” የሚል ግልፅ መፈክር ተመሳሳይ ስሜት ካላቸው ግንቦት ሰባቶችም ጋር ተቀባይነት አግኝቷል። በአማራ ደም የደቡቡ መንግስት እንተክላለን የሚለው የነብርሃኑ ነጋ፣ ኤፍሬም ማዴቦና ሰባቱ የደቡብ የግንቦት ሰባት አመራሮች ስዉር አላማ ጋር ሙሉ ለሙሉ ይገጥማል። ለዚህም ነው በኢሳት እና ሌሎች ሚድያዎች ምስክር ሆኖ እየቀረበ ያለው።

ይህንን ጉዳይ ተራ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሳይሆን ስትራቴጅያዊ የሃይል ማዛባት ፍላጎት ነው። በታሪክ ጠባሳ የታጨቀ የቁጭት አካሄድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያልታየ ገፅታ ያመጣ ይመስላል። ጠቅላይ ሚኒስቴሩንም ሆነ ደኤሄደን ይህን ሃሳብ ያራምዱ ይሆን የሚል ስጋት በብዙዎች እየተፈጠረ ነው። ይህ አደገኛ ነው። በእኩልነት የምትተዳደር ኢትዮጵያን እንደመናፈቅ በተራየ የበላይ ልሁን እሚል እንጭጭነት ትዝብት ዉስጥ ይከታል እንጂ የመሳካት እድሉ የሞተ መሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል።

አቶ አንተነህ ደግሞ የወይዘሮ አዜብን ወይም የአቶ አባይ ፀሃየን ስም በማጥፋት የሚጠፋ የትግራይ ህዝብ ታሪክ እንደሌለ ሊገነዘቡ ይገባል። የዚህ ቁጫጭ ሴረኛ የዉሸት መረጃ እየተቀባበሉ ለተለመደው ዘረኛ አላማ የሚያዉሉ ሳይማሩ የሚያስተምሩ የስዩም ተሾመ ዓይነት ግብዞች ደግሞ ሚናቸው በሰው ድርሰት የስርጭት አሻንጉሊትነት መሆኑ ተረድተው የሰው መጠቀምያ ከመሆን ቢቆጠቡ ህሊናቸው ሰላም ያገኛል።

የትግራይ ህዝብ ሌባን አይደብቅም፣ ከማንም በላይ ጠላቱም በስሙ የሚነግዱ ሰዎች መሆኑ ያዉቃል። ሌባ ብሄር የለዉም። ዘራፊ መዝረፉ ለራሱ ጥቅም ሆኖ ሳለ የብሄሩን ስምም አብሮ እንደሚጠፋ ልምዳችን ያሳያል። ኢትዮጵያ የሙሰኛ ፖለቲከኞች እንጂ ሙሰኛ ብሄር የላትም። አዲስ አበባን በልመና ያጨናነቀው ማን ሆነና? በክልሉ ስራ አጥቶ መወልወያ መጥረግያ የሚሸጠው ማን ሆነና? ቁራሌው እያለ ከተማዋን ሲዞም የሚዉል ማን ሆነና?

አቶ አባይና ወይዘሮ አዜብ እሚያስጠይቅ ጥፋት ከተገኘባቸው እንደመነኛው ኢትዮጵያዊ ሊጠየቁ ይገባል። አቶ አንተነህ እና የዉስጥ አርበኞች አባይን እና አዜብን በመታገል ስም የከፈታቹሁት ህወሓትን ገዝግዞ ብአዴንን አግልሎ የበላይ የመሆን ፍላጎት የጥፋት መንገድ መሆኑ ተገንዝባቹህ ህልዉናችንንና እኩልነታችንን ያረጋገጠለንን ፌዴራላዊ ስርዓት ለማጠናከር በጋራ እንስራ።

ይህ ህወሓትን ወይም ግለሰቦችን ጠበቃ የመሆን ጉዳይ ሳይሆን የነገሮችን ስትራቴጂክ ዓለማ የማጋለጥ ጉዳይ ነው። ዉሻ በቀደደው ጅብ ይገባል ነዉና ነገሩ ያልተገመቱ ሃይሎች ጥምረት ፈጥረው አደጋ እንዳይጋርጡ ማስተዋል ይገባል።

  1. ጉዳዩ ከፍየል በላይ ነው!.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *