13 የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸዉ ለአርበኞች ግንቦት7 እጃቸዉን ሰጡ!!!

#Ethiopia : አርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጵያ እዝ! የአግ7 በተደጋጋሚ ሲገልፅ እንደቆየው ፀቡ እና ችግሩ ከስርዓቱ ጋር እንጂ ስርዓቱን ያለፍላጎታቸው ተገደው ከሚያገለግሉት አካላት ጋር አለመሆኑን በመግለፅ ድርጅቱ ባደረገው ጥሪ መሰረት 13 የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸዉ ለአርበኞች ግንቦት7 እጃቸዉን ሰጥተዋል። ወታደሮቹ የያዙት መሣሪያም 1ብሬን መትረየስ፡ 2-ስናይፐር፡ 10 ክላሻ መሳሪያና በርካታ ጥይቶች እንዲሁም 2 የወታደራዊ ራዲዮ መገናኛ ጨምሮ ለአርበኞች ግንቦት 7 ማስረከባቸው ታውቋል። እኛ የወያኔ ዘረኛ ሥርዓት ለማስቀጠል የገዛ ሕዝባችን አንገልም በማለት ወደ ትግል ሜዳዉ ተቀላቅለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ የመከላከያ ሰራዊት የወያኔን ስርአት እየከዳ እንደሆነ ይታወቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *