የፋሲል ደሞዝ አዲስ ነጠላ ዜማ —————— ” ይለፈኝ “

የፋሲል ደሞዝ አዲስ ነጠላ ዜማ
——————
” ይለፈኝ ”
————
ኧረ ኧረ ለምን ጦም አድሬ
አልሞትም ከነሙሉ ክብሬ
በልቼው ገብቶ ከሚያቅረኝ
ግዴለም ይለፈኝ ይዝለለኝ
ኧረ ረ ኧረረረ
ፉት ቢሏት ጭልጥ ፤ ለምትለው እድሜ እንጀራስ አልበላም፤ ወንድሜ ላይ ቁሜ
እንዲህ ያለጊዜ፤አሽሙረኛዘመን
የተበላው ፋፍቶ፤ የበላው መመንመን ።
ዘራፍ እያለ
ሌባ እንደማስጣል
እየዘረፈ
ይመጠምጣል
እሪያ ባመሉ
ሰው ነው በገላው
ወጥ ነክቷል ብሎ
ጫማውን በላው
ኧረ ረ ኧረረረ // አዝ
ሁሉን ለኔ ለኔ አልልም
ሁሉን ለኔ ለራሴ
አፈር እንጅ ወርቅ አይሆንም
መቼም ስሞት ትራሴ
ክብር እምነት እያስጣለ
የተተፋ ሚያስልሰው
ኧረ ምነው ምነው
ኧረ ምን ነክቶታል ሰው
ኧረ ምን ነክቶታል ሰው
ኧረ ምን ነክቶታል ሰው።
ኧረ ኧኧኧረረረ // አዝ
አፈር ስሆንልህ በል እዳትጨርሰው ፣
ድህነት አይፈራም እንደኔ አይነቱ ሰው ።
እንዲህ አይነት ነገር ባፍንጫዬ ይውጣ ፣
ገንዘብ ገንዘብ እንጅ ፍቅር አያመጣ
ስንተኛ እንደሆነ አያውቁንም እንጅ
ሊሞት ተሰልፏል ሁሉም የሰው ልጅ
ፍቅር የሌለው
ወይ የሰው መውደድ
ወገቤን ይላል
ከመሃል መንገድ
እንዳሳዩት ነው
ሆድና ፊት
እኔስ ለፍቅር
ለሰው ልሙት // 6x
ሁሉን ለኔ ለኔ አልልም
ሁሉን ለኔ ለራሴ
አፈር እንጅ ወርቅ አይሆንም
መቼም ስሞት ትራሴ
ክብር እምነት እያስጣለ
የተተፋ ሚያስልሰው
ኧረ ምነው ምነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *