በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተገለው የተገኙት ተመራቂ ተማሪዎች ጉዳይ ወጥረት እንዳያስነሳ ተፈርቷል፡

BREAKING ….#Mekeleuniversity

በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተገለው የተገኙት ተመራቂ ተማሪዎች ጉዳይ ወጥረት እንዳያስነሳ ተፈርቷል፡፡ መቀሌ ድረስ ልጆቻቸውን ለማስመረቅ የሔዱ ወላጆች የልጆቻቸውን አስከሬን ተቀበሉ ተብለዋል፡፡ ከምንም በላይ አነጋጋሪ የሆነው ደግሞ ስድስቱም ሟቾች በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡና ሁሉም የአማራ ብሔርር ተወላጆች መሆኑን ተገልጿል፡፡ አንደኛው ሟች የማዕረግ ተመራቂ ሲሆን ባገኘው የስኮላርሺፕ እድል ወደውጪ ለመውጣት ቅድመሁኔታዎችን የጨረሰ መሆኑ ታውቋል፡፡ አንዱ ሟች ዛሬ በባህርዳር የቀብር ስነስርዓቱ የተፈፀመ ሲሆን ወላጆች ስለልጃቸው አሟሟት ቢጠይቁም በመንግስት አካላት ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው በሀዘን ገልፀዋል፡፡

የሟቾችን ዝርዝር ከነፎቶግራፋቸው ቤተሰቦቻቸውን በማስፈቀድ በቅርቡ እንለቃለን፡፡

ምናልባት ተመራቂ ልጅ የጠፋባቸው ወላጆች ስለሚኑሩ ይህን ፅሑፍ ለሌሎች ብታጋሩ መልካም ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *