ማንም የማይመልሰዉ ፈጣሪ መጣ! ዝሆኑ ወድቋል አሁን ለመነሳት እየተፍጨረጨረ ነዉ

ማንም የማይመልሰዉ ፈጣሪ መጣ!
ዝሆኑ ወድቋል አሁን ለመነሳት እየተፍጨረጨረ ነዉ የሉም ሲላቸዉ የነበሩት የአርበኛ ልጆች ከዉስጥም ከዉጪም እያነደዱት ነዉ አሉኝ ሲላቸዉ የነበሩት ሁሉ በመፈርጠጥ ላይ ናቸዉ አድፍጦ ሲጠብቅ የነበረ ሁሉ ወደ ዝሆኑ እየተግተለተለ ጉረኛዉን በመቀጥቀጥ ላይ ይገኛል።
ቀን መጣ ለእነርሱ ክፉ ቀን ለኛ ደግሞ የነጻነት ብርሃን ይዞ እየደረሰ ነዉ።
እስር ቤት ሲገነቡ እኛን ለማፈን ነበር ሲገድሉም እኛን ለማዳፈን ነበር ሲያሳድዱን እነርሱ ለመኖር ነበር ግን ቀን መጣ ያፈጠጠ ቀን ደረሰ ስንጠብቀዉ የነበረ ቀን በሰሩት እስር ቤት ዉስጥ የሚቆለፍባቸዉ የኛ የእዉነት ዳኝነት የሚፈርድበት ቀን።
ተከፋፍሎ እእርስ በእርሱ እንዲጫረስ ተፈርዶበት የነበረዉ ህዝብ መጣ! ሐብቱንና ንብረቱ ጥሎ የተሰደደዉ ህዝብ መጣ! ልጆቹ ለሰሐራ በረሐ ግብር የተሰጡበት ህዝብ መጣ! ልጆቹ ለሊቢያ የቢላ እራት የተሰጡበት ህዝብ መጣ! ልጆቹ ለእሩቅ ምስራቃዊያን ለስጋ ፍትወት ለመከራና ለፍዳ የተሰጡበት ህዝብ መጣ! በገዛ ሐገር ልኑር ሲል ካልከፈልክ አትኖርም የተባለዉ ህዝብ መጣ!
ያነባዉ የቃተተዉ ህዝብ መጣ!
አባቱንና እናቱን የተነጠቀዉ ህዝብ መጣ!
የተዋረደዉ የተሰደበዉ ሐይማኖቱን የተነጠቀዉ ሐገሩን ክብሩን ባንዲራዉን የተወረሰ ህዝብ መጣ!
አጥፍተነዋል አከርካሪዉን ሰብረነዋል ከእንግዲህ አይነሳም የተባለዉ ህዝብ መጣ!
የተቀለደበት በየፓርላማዉ ላይ የተሰደበዉ ህዝብ መጣ!
የለም የተባለዉ ህዝብ መጣ!
የተናቀዉ መጣ!
አይመጣም ያሉት ቀን መጣ ደረሰ ።
እንግዲህ ፈጣሪ ካመጣዉ ከቶ ማን ይመልሰዋል?
ምንም አይመልሰዉም!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *