የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው

  1. #ETHIOPIA | የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው❗️

በማንኛውም መንገድና ሰዓት በወያኔ አፓርታይድ ስርዓት ላይ ለሚከፈትበት ጦርነት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አያገባውም እንዲያውም በሌላው መንገድ ጦርነቱ በወያኔ ተሸናፊነት እንዲጠናቀቅ የመላው ኢትዮጵያውያን ፍላጎት እንደሆነ አምናለሁ ። ይህንንም የምልበት ምክንያት ከፖለቲካ ጥላቻ ተነስቼ ሳይሆን ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ስለሆነ ነው ።

የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ባለፉት 26 ዓመታት በወያኔ አፓርታይድ ስርዓት የደረሰበትን ግፍና መከራ ተዘርዝሮ የሚያበቃ አይደለም ። ማንኛውም የውጪ ወራሪ ጠላት ከሚያደርግብን ወይም ሊያደርግብን ይችላል ብለን ከምናስበው በላይ በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ጥቃት ብቻ ሳይሆን ኢሰባዊ ድርጊቶች ተፈፅመውብናል። እነዚህም ኢሰብአዊ ድርጊቶች የተፈፀመባቸው ግለሰቦች ወይም ደግሞ አሁንም እየተፈፀመባቸው ያሉት ኢትዮጵያውያኖች በሰሩት ወንጀላቸው ወይም ደግሞ ጥፋታቸው ሳይሆን በማንነታቸው እና በአመለካከታቸው ምክንያት ብቻ ነው ።

የወያኔ አፓርታይድ ስርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ህዝቦችን እርስ በእርስ ማጋጨት ማንነታቸውን እና ስብዕናቸውን ማዋረድ ዋነኛው ተግባሩ ከመሆኑም በላይ የአገሪቱን ሃብትና ንብረት ዘርፎ ህዝቡን ወደ ድህነት ማቅ ውስጥ በመክተት ብሄራዊ ውርደትን ያከናነበን ስርዓት ጭምር መሆኑን ሊዘነጋ አይገባም ።

ስለሆነም ይህንን ስርዓት በማንኛውም መንገድ ለሚመጣበት ጠላት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አያገባውም እንዲያውም በዚህ ጠላት ላይ የሚነሳበት ጠላት የእኛ የኢትዮጵያውያኖች ወዳጅ ሊሆን ነው የሚገባው ። እናም ዛሬ በወያኔ አፓርታይድ ስርዓት የከፈተው ጦርነት ኢትዮጵያውያንን የሚመለከት ሳይሆን እራሱን ወያኔን የሚመለከት ብቻ ነው ።

እንዲያውም መላው ኢትዮጵያውያን ይህንን በወያኔ ስርዓት የከፈተውን ጦርነት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመን ወያኔን ከስሩ መንግለን ለመጣል ሁላችንም በአንድነት ልንነሳ ይገባናል ። ይህ ስርዓት ቀንና ጊዜ ባገኘ ቁጥር ኢትዮጵያውያንን ከማሰቃየትና ከመግደል ወደኋላ እንደማይል ሁላችንም ጠንቅቀን የምናውቀው ነው ። ስለሆነም መላው ኢትዮጵያዊ ወያኔን ለመጣል ሁሉም በየአካባቢው በመደራጀት ከመሃል እስከ ዳር ሁሉም ተዘጋጅቶ ለትግሉ ይቁም ።

ለኢትዮጵያ ህዝብ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ጠላቱ ወያኔ ነው ።

ዘነበ ዘ ቂርቆስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *