በህወሓት አፍኝ ቡድን ታፍነው የነበሩት ባህታዊ አባ ብርሃኑ ከፍርድ ቤት ቀጠሯቸው ቀድሞ ከእስር ተፈቱ!

 1. በህወሓት አፍኝ ቡድን ታፍነው የነበሩት ባህታዊ አባ ብርሃኑ ከፍርድ ቤት ቀጠሯቸው ቀድሞ ከእስር ተፈቱ!
  የህወሓት ቡድን ሽንፈት ተጎንጭቷል ፤ የቴሌቪዥን ታወር ያሉት ግንባታ ሁሉም ባለበት ቁሟል!!
  የደብረታቦር ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ቁጣውን ተናግሯል !!
  በዛሬው ሐምሌ 12 ቀን 2009 ዓ.ም በደብረታቦር ኢየሱስ ደብር ማንም ከቤቱ የቀረ አልነበረም የግፍ ቁጣ በውስጡ የሚብላላ ሁሉ ሱቁን ፣ሆቴሉን ዘግቶ ወደ ታቦር ተራራ በህብረት ሲተም ነበር። በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራው ደምቆ በተጀመረው ስብሰባ የህዝቡን ቁጣ የፈራው ህወሃት ቀድሞ ከትናንት በስቲያ ከሰአት በፈታቸው ባህታዊ አባ ብርሃኑ ህዝቡን በስርዓቱ ካስቀመጡ በኋላ በድምፃቸው ብቻ (ያለ ድምፅ ማጉያ ) << የሚሉትን ስሟቸው ከዛ መልሱን እንመልሳለን ያጠፋ ይመለሳል ፤ እኛ ከሆነ ያጠፋነ እንመለሳለን እነሱም ከሆኑ ይመለሳሉ ካለባለዚያ የፈለገው ቢመጣ ኢየሱስ ላይ የመግስት ተቋም አይሰራም >> በማለት የእግዚአብሔርን ቃል በማሀል በማሀል እያስተማሩ ህዝቡን እያነቃቁት ተጀመረ። ህዝቡም በተመረጡ ሰወች ብሶቱን ተናገረ። የከተማው የህወሓት ተወካይ ከንቲባ ታደሰ ህዝቡን ለማሳመን ሲታትር የቆየ ሲሆን በመጨረሻም የህዝቡ ቁጣ ሲበረታ ሁሉም ባለበት ሊቆም ተወስኖ ይሄን ታወር የሚያስገነባው የፌድራል መንግስት ስለሆነ ህዝቡ እምቢኝ አልፈልግም ብሏል ብየ ሪፓርት አቀርባለሁ በማለት ተመልሷል።
  የአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራ በህወሓት ካድሬወች እንደማይፈቀድ ቢታወቅም ዛሬ ደብሩ ደምቆ አሸብርቆ ነበር የዋለው። መቼም ከቤተክርስቲያን እንደማይለያይ እና ኮከብ ያለውን ሳይጣናዊ አርማ ከዚህ አንሰቅልም በማለት አንድ ዳኛ በከፍተኛ ድምፅ ሲናገር ተሰምቷል።በግንባታ ቦታው ሰምጠው የቀሩት አንድ ሲኖተራክ መኪና አሽዋውን ለደብሩ በስለት አስገብቶ ሊወጣ ችሏል። ሲኖትራኩን ሊያወጣ የገባው ክሪክ ከዛው ሰምጦ ይገኛል። በፈጣሪ ሃይል የታሰሩትን ጨምሮ በፎቶው አባ ብርሃኑ የቆሙበት መኪና ከትናንት ምሽት ጀምሮ ባሉበት እንዲቆሙ ተደርጓል።
  በደብረታቦር ከተማ በዚህ እና አግባብ ባልሆነው የግብር ተመን ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች። አንዳች የሚፈነዳ ነገር አንዣቧል። በከተማዋ በመውጫ መግቢያው ጨምሮ ብዛት ያለው የልዩ ሃይል አድማ በታኝ ወታደር ተወራ ትገኛለች!!
  ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው !!
  @እንቅዩጳዝዩን የአርበኞቹ ልጂ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *