ወያኔ የማይችለው ውጊያ! ኢኮኖሚ!

ወያኔ የማይችለው ውጊያ! ኢኮኖሚ!

ይህን ያክል የጠነከረና ያልቆመ የህዝብ ተቃውሞ ሲያምሰው የከረመው ወያኔ በገንዘብ ድርቅ ምን ያክል እንደተመታ ግልፅ ነው።

አንደኛ) በመላው ሃገራችን ያሉት ዶላር የሚያስገቡ የእርሻና የፋብሪካ ውጤቶች ተንኮታኩተውበታል።

ሁለተኛ) ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት በመኖሩ የንግዱ ማህበረሰብ መነገድ የማይችልበት ፋብሪካወችም የጥሬ እቃ ማስገባት የማይችሉበት ደረጃ ከደረሱ ቆዩ።

ሶስተኛ) ከፍተኛ የኤሌክትሪክ እና የነዳጅ እጥረት በመኖሩ በአጠቃላይ የንግድና የምርት ውጤት ላይ ከባድ ኪሳራ አድርሷል።

አራተኛ) የወያኔ የንግድ ድርጅቶችን ውጤት ያለመጠቀሙ ውጤት/boycott ወያኔን ወገቡን ሰብሮታል። ምሳሌ ዳሸን ቢራ!

አምስተኛ) የአለም አቀፍ ብድር በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሏል። ለጋሽ ሃገሮችም እጃቸውን እየሰበሰቡ ነው። አሜሪካ፣ እንግሊዝና አውሮፓ ህብረትን በአብይነት እንጥቀስ።

ውጤት፦
1) ትግሉ በመራዘሙ ወያኔ ወደ ማይቀረው ሽንፈት ደርሷል!
2) ከፍተኛ የበጀት እጥረት በማጋጠሙ በጥቅም የተያዘው ካድሬ አበሉንና ጥቅሙን አጥቷል። ደሞዙን ወዳለማግኘት እየደረሰ ነው። እናም ለወያኔ መውደቅ ደንታ ቢስ ካድሬ ታቅፎ መቅረቱን በኦሮሞውና በአማራው አካባቢ ግልፅ ሆኗል!
3) የተራዘመው የአፈና ዘመቻ የፀጥታ አካሉ በተለይ የክልል ልዩ ሃይልና ፖሊስ ከጥያቄ አልፈው ወደ ተቃዋሚነት እየደረሰ ነው። የህወሃት የበላይነት እንደዚህ ተደርምሶ አያውቅም። ገዱን እንኳን መፈንገል አልቻሉም።
4) ይህንን እጅግ የጠላቸውን ህዝብ ማባበል ሲገባቸው በገንዘብ ድርቅ ስለተመቱ የቀቢፀ ተስፋ የግብር ቁለላ ላይ ደርሰዋል። ይህም አዲስ ዙር ህዝባዊ አመፅ በመላ ሃገሪቷል ቀስቅሷል። ይህም የተራዘመ ጦርነቱ የወያኔን ተሸናፊነት አብሳሪ ሆኗል። ይህን ድል በተገቢው ማንፀባረቅ ይገባናል።
5) ይህ የሚወስደን የወያኔን እራሱን ጠልፎ መጣል ነው። ምክንያት አማራጫቸውን አሟጠው ጨርሰዋል። ከህዝቡ የሚጠበቀው ትግሉ ውጤት እያመጣ ነውና ግፋ በለው!
6) የመጨረሻው ደረጃ ለድህረ ወያኔ በቅጡ መዘጋጀት ነው። ሃገራዊ ራእይ መንደፍ! ህዝባዊ መንግስት መመስረት! በእኩልነት ላይ የተመሰረተች የህግ የበላይነት የሰፈነባት፣ የጋራ ሃገር መገንባት! ኢትዮጵያን የምትሉ በቅንነት ተሰባሰቡ! ይህችን ፅሁፍ ከአንድ አመት ስታነቧት ምን እንደሚሆን በእዝነ ልቦና አስቧት! ትርጉም ከሰጠችም ለወዳጅ ወገን ያጋሯት ያራቧት! እግዜር ይጨመርበት!
Asnakew Abebe

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *