ሰበር ዜና !!!!!

ሰበር_ዜና
===========================
የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬች የወያኔ ማሰቃያ ክፍልን አቃጠሉ።
***
ሀምሌ 10 ቀን 2009ዓ/ም ከምሽቱ 4:00 ሳዓት ላይ በሰሜን ጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኘውን ወያኔ “ሴፍ ሀውስ” እያለ የሚጠራውን ንፁሃንን የሚያሰቃይበት ክፍል መሉ በሙሉ እዲጋይ ተደርጓል። ይህ ክፍል በውጭ ሲታይ መኖሪያ ቤት የሚመስል ሲሆን ለሽፋን ያመች ዘንድ በህወኃቱ የደህንነት አባል በሙሊጊታ ግርማይ ስም የተገነባ ሲሆን ሙሊጊታ ግርማይ ደግሞ ሰላይ መሆኑ እዳይታወቅበት በነጋዴ እና በሽፌርነት ሽፋን ተዘጋጅቶለት በርካታ ንፁሃንን በማስገደል፣በማሳፈን፣አብሮ የታሰሩ ሰዎችን ወደ ትግራይ እና ማዐከላዊ በማጓጓዝ ፣ ማታ ማታ የራሱን ቅርፅ በመለዋወጥ የመከላከያ ልብሶችን በመልበስ በርካቶችን አሳፍሳል። በዚህ ክፍል ላይ በርካቶች እደሚሰቃዩ እና በጨለማ ጩሆት እደሚሰማ ቦታው ወጣ ያለ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት ጎን በመሆኑ ዘበኞች በተደጓጓሜ በጨለማ ወታደራዊ መኪናዎች በዚህ ቤት ላይ ሲወጡና ሲገቡ እዳያቸው ጥቆማዎችን በመስጠታቸው ይህ ጥቆማ ለአግ7 በመድረሱ፣ ድርጅቱም በዚህ የማሰቃያ ክፍል ውስጥ እርምጃ መወሰድ እዳለበት እቅድ ወጥቶለት እቅድ በወጣ በ33 ቀን በትናንትናው ቀን ዘመቻው በተሳካ መንገድ ተከናውናል። ይህ ዘመቻ በዜና ሲወጣ ቀላል ይመስላል በመሆኑም ዘመቻው ለምን 33 ቀናትን መጠበቅ አስፈለገ? በዚህ ክፍል የማሰቃየቱን ስራ እነማን ይፈፅሙ መበር? ዘመቻውን በፈፀሙት እና ዘመቻውን ይመሪ በነበሩ አመራሮች ላይ የነበረው ፈተና ምን ነበር? የስቃዩ ሰለባዎች እነማን ነበሩ? የህብረተሰቡ ተሳትፎስ ምን ነበር? የሚሉትን እና ሊሎችን በዝርዝር መግለፅ አስፈላጊ በመሆኑ ከባለፈው የአዲስ አበባ ዘመቻ ጋር ተያይዞ በርካታ የማሰቃያ ክፍሎች በተለያዩ የአገራችን ቦታዎች መኖራቸው በጥቆማ እየመጡ በመሆኑ ህዝባችን እዲያውቀው እና አስፈላጊውን እዲያደርግ የሚረዳ መሆኑን በመገንዘብ ዝርዝሩን እፅፋለን።

የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ
ጠላትን ማጥቃቱ ይቀጥላል !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *