የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም፤ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት”

የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም፤ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት”

እውነቱን ለመናገር ልዩ ጥቅም ብሎ ነገር ሃሳቡ ራሱ ፉርሽ ነው! በአንድ ሃገር ላይ አንዱ ከሌላው ተለይቶ ልዩ ጥቅም ያግኝ ብሎ እንዴት ህግ ይደነገጋል? እኩል ጥቅም ማስገኘት ያባት ነው! ልዩ ጥቅም ምንድነው… ? የህግ መሰረታዊው አንቀጽ “ሰው ሁሉ በህግ ፊት እኩል ነው” የሚል ነው።

በሰለጠኑት ሃገራት አንዳንድ ሰዎች Special need /ልዩ ፍላጎት/ ያላቸው ተብለው ከመደበኛው ሰው በተለየ እንክብካቤ እና ጥበቃ ይደረግላቸዋል። እነርሱም በተፈጥሮ ወይም በአደጋ የአካል ወይም የአዕምሮ ጉዳት የገጠማቸው ሰዎች ናቸው። ኦሮሚያ ምን ሆና ነው ልዩ ጥቅም ያስፈልጋታል የምትባለው! ገለታ ዋቃ እጅ እግር ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ነዋሪዎች አሏት።

ባለፉት ግዜያት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተደረጉት ተቃውሞዎች እኩል ተጠቃሚነትን የሚጠይቁ እንጂ ልዩ ተጠቃሚነትን የሚጠይቁ አልመሰለኝም! ነህዝቦች መካከል ልዩ ተጠቃሚ መጠነኛ ተጠቃሚ ብሎ ለህዝቦች ደረጃ ማውጣት እርስ በርሳችን እንድንባላ ታስቦ ካልሆነ በቀረ ሌላ አላማ አለው ብዬ አላምንም! እደግመዋለሁ እኛ የምንፈልገው እኩል ተጠቃሚነትን እንጂ ልዩ ተጠቃሚነትን አይደለም! የህጉ አርቃቂዎችም ይችን ስታረቁ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት” አይነት ነው እንጂ ለኦሮሞ ልዩ ጥቅም ልትሰጡ አይደለም! (አራት ነጥብ አሉ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከመለስ ዜናዊ ቀድተው…. (ከነርሱ ከምቀዳ ብዬ ንግግሬን በቃል አጋኖ ዘግቻለሁ))

ከአበበ ቶላ ፈይሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *