ዘጠኝ የሱዳን ወታደሮች ተገደሉ!

ሰበር ዜና
♦ዘጠኝ የሱዳን ወታደሮች ተገደሉ!
♦ወያኔ በወልቃይት ባህረሰላም ሃይል አንቀሳቀሰ!
♦በሁመራና አርማጭሆ የተደረገው የእርቅ ሙከራ ከሸፈ!
ሰኔ 7 2009

በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር በሁመራ መስመር ከወያኔ መሬታችንን ለመረከብ የገቡ 9 የሱዳን ወታደሮች በጎበዝ አለቆች እርምጃ ተወሰደባቸው። በወያኔ አጀብ በሁመራ መስመር የገባው የሱዳን ሃይል ተበታትኗል።

በወልቃይት ባህረ ሰላም በኩል ደግሞ ወያኔ ወደ ኤርትራ በኩል ሰራዊት እያንቀሳቀሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ያልተለመደ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በቀጠናው እንደሰፈነ ኗሪዎች ጋልፀዋል። ይህ አካባቢ ወደ ኤርትራ ድንበር ጥግ ነው።

ወያኔ ሁመራና አርማጭሆ ላይ ያደረገው ላሞኛቹህ የእርቅ ሙከራ ከሸፈ። ሸማግሌዎች የተባሉት ብዛት 16 ሲሆኑ አብራሃጅራ ላይ አሰማራዉ መኮነን የተባለ የወያኔ ተላላኪ፣ አብደራፊ ላይ ዋኘዉ አቡሃይ፣ ፋሲል አሻግሬ፣ አድምጠዉ ታደሰ ሲሆኑ ዳንሻ ላይ የወያኔ አሽከር የሆነ በገዘብ ትግሬ ነኝ የሚል ካህሳይ ሐብቱ ከ1986 ጀምሮ የወልቃይትና የጠገዴ ተወላጆች በገዘብ እየተገዛ ካሰገደለ በኋላ ወያኔ የቀጠሩት ነው። እሱ እና ሌላው ሹምየ የተባሉት በሃገሬው ህዝብ ተከዜ ወዲህ ቤት እዳትሰሩ ተብለዉ የተወገዙ በመሆኑ ትግራይ ሄደው ቤት የሰሩ ናቸዉ። የጎንደርን ሕዝብ ወክለው በምንም መልኩ ከትግሬወች ጋር ሊነጋገሩ አይችሉም። ይልቅ የአርማጭሆ ህዝብ ለምትገሏቸው ወንድሞቻችን ሃላፊነት ውሰዱ፣ የአሰራቹሃቸውን ወገኖቻችንን ኮለኔል ደመቀን ከነ ወልቃይት ኮሚቴወች በሙሉ ፍቱ፣ መሬታችንን ልቀቁ፣ ማንነታችንን አክብሩ ብለው እቅጩን ነግረዋቸዋል።

ሁመራ ላይ በተደረገው የእርቅ ድራማ ደግሞ የተገኙት በሙሉ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ ወልቃይቴወች አልተገኙም። የስብሰባው መሪ የሆነው የወያኔ ሹም ህዝቡ ከወልቃይቴወችና ጠገድቸወች ጋር የማለሳለስ ስራ እንድትሰሩ ሲላቸው በአንድ ወላጁ ግማሽ ወልቃይቴ የሆነ ወጣት መንግስት የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ እሮሮ መስማት ሲገባቹህ የእናንተ አፈና ነው ይህን ችግር ያመጣው ብሎ በድፍረት ተናግሯል። በአጠቃላይ ወያኔ በእርቅ ስም የህዝቡን ትግል ለመቀልበስ የሞከረው ሙከራ ከሽፏል።

የጎንደር ህዝብ ወልቃይት ላይ ከ1972 ጀምሮ ከዛ ቆላማው ወገራ ከ1974 ጀምሮ ዳባት ላይ ደግሞ ከ1977 ጀምሮ አብዛኛው የጎንደር ቦታ ላይ እስከ 1983 ከወያኔ ጋር እጅግ ዘግናኝ ጦርነት ሲያደርግ ኖሯል። አሁን ደግሞ ፀረ ወያኔ ትግሉ ስልቱን እየቀያየረ ጎንደር ላይ ሳይቋረጥ ከሃምሌ 5 2008 ከጀመሬ ድፍን አንድ አመት ሞላው።
Asnakew Abebe

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *