ልማታዊ ካድሬ የፓስተር ዳዊት ተረተረት !

ፓስተር የኛ አገር አክተር

ፓስተር ዳዊት ፤ ቴዎድሮስ ኣድሓኖም ከሰማይ በሰበር ዜና እንደሚመረጥ ከሁለት ሰማንት በፊት ተናግሬ ነበር በማለት ሰሞኑን ተናግሯል ። የፓስተር ዳዊት ጌታ የምርጫ እና የበርጫ ጌታ እንደሆነ ያቃቃሙት ነግረውኛል ። ለመሆኑ ጠቅላዩ በከፈን ሲጠቀለሉ ፓስተር ዳዊት ከሰማይ ሳይሆን ከዋሽንግተን ዲሲ አበበ ገላው በተባለ አንገት ሰባሪ ዜና ለህዝብ የደረሰውን እውነት እንዴት ያዩታል ? የጎሪጥ ? ፊት ለፊት ? ባፍጢማቸው ? ወይስ ሰበር ዜናውን ከገነት በሚልክላቸው ጎዳና ተዳዳሪ ጌታቸው ?
ለማንኛውም እኔ ፓስተር ዳዊት ከማለት ፖስተር ( poster ) ዳዊት ብል ጌታ አይገስፀኝም ! እንዲህ ያለው የወጣለት ዱርዬ ፥ አጥማቂ ፥ አዋቂ እና በልሳን ተናጋሪ ሆኖ ብቅ ሲል ፥ እምነት እና ኢትዮጵያዊነት ሞቷል !!!!
ኄኖክ የሺጥላ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *