ምን እንድናደርግ ይጠበቅብናል?

በኔ ግምት የወቅትቱ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ወሳኝ እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው:

1. በአገዛዙና በሕዝብ መካከል ያለው ቅራኔ ተጋግሏል። ካቢኔዎችን የዩኒበርስቲ ሴኔት ማስመሰልም ሆነ ስለ ኢኮኖሚ አብዮት ማውራት ተጨማሪ ምፀቶችን ከመፍጠር ያለፈ ፋይዳ የላቸውም።

2. በህወሓት ውስጥ እና በህወሓትና በምስለኔ ድርጅቶቹ መካከል ያለው ቅራኔ ተባብሷል።

ይህ ቢሆንም ቅራኔዎች ስለተጋጋሉ ብቻ አምባገነን አገዛዝ በአጭር ጊዜ ውስጥ አይወድቅም። አገዛዙን የሚጥለው ኃይል መኖር አለበት።

የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ እንዲወድቅ እና በተሻለ የሕዝብ አስተዳደር እንዲተካ የሚከተሉት ሥራዎች መሠራት አለባቸው

1. ከምንጊዜውም ጊዜው በላይ ህቡዕ ሕዝባዊ አደረጃጀቶች መፋጠን አለባቸው፣
2. በየቦታው ትንኮሳዎች መኖር አለባቸው፤ መረጋጋት መኖር የለበትም፣
3. በጦር ሠራዊቱ፣ በፓሊስ፣ በመረጃ መዋቅሩ፣ በመስተዳደሩ፣ በኢህአዴድ፣ በፓርላማዎች ውስጥ የአሻጥር ሥራዎችን መሥራት መለመድ ይኖርበታል፤
4. ሕዝባዊ አሻጥር፣ ሕዝባዊ ስለላ፣ የህቡዕ ጦርነት፣ የውስጥ አርበኝነት መበረታት ይኖርባቸዋል፣
5. የተደራጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነት መቀስቀስ ይኖርበታል፣ እና
6. ራሱንና ሕዝብን ከጥቃት የሚከላከል ኃይል ሊጠናከር ይገባል።

እነዚህን ሥራዎች ማከናወን የእያንዳንዳንዳችን ኃላፊነት ነው። በምናውቀውና በሚመቸን መንገድ ትግሉን እናግዝ። ይህን ካደረግን አገዛዙ ይወድቃል፤ እጅግ የተሻለ ሥርዓትም ይመጣል።

© D’r Tadesse Biru Kersmo

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *