ዘሪሁን ተሾመ ማነው ? ጭንብሉ ሲገለጥ

ዘሪሁን ተሾመ ማነው ? ጭንብሉ ሲገለጥ

መስቀሉ አየለ

ይኽ ሰው በአሁኑ ሰዓት በነጌታቸው አሰፋ አንጃ በኩል “ገኖ” የወጣ የፖለቲካ ቀመር አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ብቅ ብሏል። አገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል አይነት መሆኑ ነው። የዚህን ሰውዬ ትክክለኛ ሰብዕና በመጠኑም ቢሆን ለአንባቢያን “ከፍቶ ማሳየቱ” በጣም ወቅታዊ ነው።

ዘሪሁን ተሾመ ደብረዘይት በሚገኘው የቬተርኔሪ ሳይንስ ማሰልጠኛ ካምፓስ ውስጥ የፍልስፍና መምህር ነበር። ወያኔ ሰልጣን በያዘበት አመት የአንዲት ተማሪ ቦርሳ ሰርቆ ከዩኒቨርስቲው ተባረረ።በዚህ አይነት እርካሽ ቅሌት ያውም ፍልስፍናን ያህል በሰውና በዪኒቨርስ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመረምር የትምህርት አይነት እያስተማረ የራሱን እርካሽ ፍላጎት ለመግታት ጉልበት ያልፈጠረበት፤ በዚህም አይነት መጥፎ ስነምግባር ከዩኒቨርሲት የተባረረ ምናልባት በሰው ልጆች ታሪክ የመጀመሪያው ሰው ሳይሆን አይቀርም።

ይኽ ሰው ስራውን ከፈታ ቦሃላ ኑሮውን መደጎም ባለመቻሉ የአንድ ልጁ እናት ሴት ልጇን ጥላበት ሄደች። ገንዘብ ስለሌው ከሚያውቀው ፊሎዞፊ ወሬ እየሰፈረ በመሸጥ የሰዎች ጫት አቃቃሚ በመሆን ከሚበላ ምግብ እስከ ሲጋራ፣ ከሲጋራ እስከ ጫት ከጫትም በል ያለው እስከ ድራፍት ሲደጉሙት የሚውሉት አይነት መናኛ ሰው ሆኖ ከህይወቱ የዕለት የዕለቱን ብቻ መኖር ጀመረ። ሴት ልጁን በተመለከተ ግን ሲኖረው ዳቦ ገዝቶላት ሲገባ፤ ሳይሆንለትም ያዘነ ጎረቤት ቁራሽ እየወረወረላት ከርማ በመጨረሻም የረሃብ ጠኔ ይዞዋጽሙ ከዲክሽነሪ ላይ ሊፋቅ አንድ ሃሙስ በቀረው የኳሽወርከር (የችጋር ) በሽታ ታማ በልጅነት አረፈች። እድር ስላልነበረው የሚያውቁትም የማያውቁትም ጥቂት ኢትዮጵያዊ ይሉኝታ ያላቸውና ለነፍሴ ያሉሰዎች ከኪሳቸው ገንዘብ አዋጥተው በወዛደር አስቀበሩለት። ይኽን የሕይወት ትራጀዲ በአካል ለማየት እድሉ የነበረውና ከረጅም አመት የስደት ህይወት ወደ ኢትዮጵያ የገባው አንዳርጋቸው ጽጌ በሰአቱ ስለ አማራ ብሔርተኝነት በጻፋት መጽሃፍ በሽያጭ ከተገኘው ገንዘብ ብር ሰባት ሽህ ቆጥሮ ሰጠውና ነፍስ ዘርቶ ከሰው ተራ ሊያቆመው ሞከረ።

በመቀጠልም በወቅቱ ተመስርቶ በነበረው አቡጌዳ የሚባል የሲቪክ ተቋም ውስጥ ስራ ፈልገው ካስገቡት ውስጥ ዋናዎች ከብዙ አመት ቦሃላ የቅንጅት አመራር ሆነው ብቅ ያሉት ልሂቃን ነበሩ። ስለ ጉድ ጋቨርናንስና የድሞክራሲ ተቋማት ግንባታ የአሜሪካን መንግስት ባዘጋጀው ሴሚናር እንዲካፈልና ልምድ ቀስሞ እንዲመለስ አቡጌዳ ይኽን ሰው ወደ አሜሪካ ሲልከው በዛው ከድቶ ቀረ። ቢሆንም ወረቀት ለማግኘት ከአገር የወጣበት ሁኔታ አላመቸው በማለቱ የነበረው ብቸኛ አማራጭ የቶይ ቦይና የሹገር ማሚ ኢሞራላዊ መንገድ መከተል በመሆኑ ሚሚ ስብሃቱ የተባለች የእነጨት ሽበት ያገባው በዚሁ ስሌት ነበር።

ከጥቂት አመታት ቆይታ ቦሃላ ባልና ሚስቱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በዋናነት በመርጫ ዘጠና ሰባት ሰሞን ኢፍቲን የሚባል ጋዜጣ በማዘጋጀት ቅንጅትን በማፍረስም ሆነ በፊት አቡጌዳ ውስጥ እንዲገባ እድል የፈጠሩለትን ሰዎች ሁሉ በማሰለል ብሎም በጋዜጣ ላይ በመወንጀል እንዲታሰሩና እንዲሰደዱ አፍራሽ ሚና ተጫውቷል።

በመቀጠልም የብሮድካስቲንግ አዋጅ ወጣ በተባለ ማግስት የተወሰነ የግል ሬዲዮ ይቋቋም ሲባል ከህወሃት በተሰጣቸው አስራ አምስት ሚሊዮን ብር በጀት ከሚስቱ ጋር የዛሚን ሬዲዮ ጀመሩ። ይሕ ጣቢያ ዛሬም ድረስ ከጀርባውከወያኔ ከፍተኛ የበጀት ድጎማ የሚደረግለት እንዲሁም እንደ ሌሎቹ የግል ሬዲዮ ለብሮድካስቲንግ ኤጀንሲው ገንዘብ የማይከፍል፣ ከህግ በላይ የሆነ በቸኛውና ሬዲዮጣቢያ ነው። ዛሬ እነጌ ታቸው አሰፋ ማንንም ሰው መምታት ሲፈልጉ በዚህ ሬዲዮ አስቀድመው በከፈተኛ ደረጃ የስም ማጠልሸት ስራ የሚሰሩበት በግልጽ አነጋገር የወያኔ የስለላ ድርጅት አፍ ሆኖ የሚያገለግል መርዘኛ ተቁውዋም ነው።
የብሮድካስቲን ኤጀንሲው ምንም እንኩዋን ከነሳሞራ በሚደረግበት ግፊት የዚህን ሬዲዮ ጣቢያ ፈቃድ ለመንጠቅ ቢሞክርም ሳይሳካለት እስካሁን አልተሳካለትም።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን ታፍነው በመጡ ሰሞን ይኽ ነውረኛ ሰው በቴሌቪዥን ቀርቦ ስለ እርሳቸው “አደገኛነትና” መንግስት ስለወሰደው ሃላፊነት የተሞላበት እርምጃ በኩራት ሲናገር ለሰማው ሰው ክርስቶስ እንደገና በመዋእለ ስጋዌ ቢገለጥ መጻጉን ሆኖ በጥፊ ለመማታት ይሁዳን ሆኖ በሰላሳ ዲናር ለመሸጥ ከዘሪሁን ተሾመ የተሻለ የሞራል እጢው በውስጡ የጨነገፈበት ቅሌታም እንዳልተፈጠረ ይረዳዋል።

ይኽ ሰው አሁን በተጀመረው የጥልቅ ተሃድሶ የመበላላት አብዮት ጉባኤ ላይ ተገኝቶ እንደ ተናገረው ወያኔ መቶ ፐርሰንት ወንበር መያዘ ብቻ ሳይሆን የሰበሰባቸው መናጆዎች ሁሉ ሳያነቡ የሚፈርሙ እና አገሪቱ ላይምን እየተካሄደ እንደሆነ እንኩዋን የማያውቁ መሆናቸው፤ በዚህም የተነሳ የሚንስትሮች ምክር ቤት እራሱ ሃይ ባይ የሌለው ያልተገራ ፈረስ በመሆኑ ለነገ ልጆቻችን ብቻ ሳይሆን እራሳችን ዛሬ ላለንበት ዋስትና የሚበጀው ብቸኛው መፍትሄ ፓርላማውንም ሆነ የሚንስትሮች ምክር ቤትን በአስቸኳይ ጠራርጎ ማባረር ነው የሚል የጥናት ውጤት አቅርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *