ጎንደር ከተማ ሄቴል ላይ የቦንብ ፍንዳታ ደርሷል…. ይህ በከተማዋ ለሶስተኛ ጊዜ የደረሰ ጥቃት ነው 4 ወር የተራዘመውን የአስቸኳይ አዋጅ ማጀቢያ ይሆን?

ጎንደር ከተማ ሄቴል ላይ የቦንብ ፍንዳታ ደርሷል….
ይህ በከተማዋ ለሶስተኛ ጊዜ የደረሰ ጥቃት ነው
4 ወር የተራዘመውን የአስቸኳይ አዋጅ ማጀቢያ ይሆን?

ጎንደር ከተማ ላይ የሚገኘው ባለ 3 ኮከቡ Florida International Hotel ትናንት ምሽት በደረሰበት የፈንጅ አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ 3 ሰወች የተጎዱ ሲሆን የሞተ ሰው ስለመኖሩ አልተገለፀም። ሆቴሉ ላይ የመስታውት መሰባበርና መጠነኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ገልፀውልናል።
አካባቢው በከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር ስር ነው። ሆቴሉ ጉምቱ የገዢው ቡድን ባለስልጣናት ስብሰባ የሚያደርጉበት ሲሆን ቱሪስቶችም ያዘወትሩታል። በቅርብ ጊዜያት ጎንደር ከተማ የፈንጅ ጥቃቶች እየተበራከቱ ሲመጡ ይህኛው ለሶስተኛ ጊዜ ነው። የጥቃቱ ኢላማወች ሁለቱ ሆቴል ሲሆኑ አንዱ የመዝናኛ ቦታ ነው።

ከወያኔ የቀደመ እኩይ ባህርይ በመነሳት ይህን ጥቃት የሚያደርገው ገዥው ቡድን ስለመሆኑ ጎንደር ውስጥ በስፋት እየተወራ ሲሆን ወያኔ በተቃዋሚ ያላክካል። 4 ወር የተራዘመውን የአስቸኳይ አዋጅ ማጀቢያ ይሆን ብሎም ማጠየቅ ይቻላል። ሃላፊነቱን እስካሁን የወሰደ አካል ባይኖርም የወያኔ የጦር መኮንኖች ጎንደር ከእጃችን ወጥታለች ማለታቸው ይህ አንዱ ማሳያ ነው።
Asnakew Abebe
~~~~~~~~~~~
Florida International Hotel Struck by a Hand Grenade፦ Gonder, Ethiopia
April 2 2017

Late saturday evening a hand grenade blasted at the 3 star ranked Florida International Hotel located in the 16th Century Capital of Ethiopia, Gonder City. Coined as the Camelot of Africa Gonder is no more enjoying the usual outpouring visit of tourists. It rather is the frontier of resistance against the brutal Tigray Minority controlled Ethiopian regime.
This hand grenade attack in Gonder is the third of its kind in recent months.

Three individuals are reported to sustain injury. There is no known fatality. The hotel sustained minor damages. Broken glasses can be seen around the premises.

The ruling regime blames the opposition for the attacks while the public at large strongly suspects the dubious hand of the regime itself. The 6 month long State of Emergency Decree just got extended by 4 months. The regime completely lost any mandate whatsoever. Learning from repeated past intelligence reports, it is only reasonable to suspect the hand of the regime to perpetrate such attacks in order to claim rotten legitimacy.

Reported by,
Asnakew Abebe

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *