በፍቅረ አዲስ ነቃጥበብ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ታዳሚ እንዳይገኝ በቴላቪቭ ቦይኮት ተጠራ !!!!!

በፍቅረ አዲስ ነቃጥበብ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ታዳሚ እንዳይገኝ በቴላቪቭ ቦይኮት ተጠራ !!!!!
*በዚህ በያዝነው በኢትዮጲያውያን አመት 2009 ዓ•ም• የዘመን መለወጫ ላይ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ አብዛኞቹ ድምጻውያኖቻችን ወያኔ በግፍ የጨፈጨፋቸውንና እየጨፈጨፋቸው ያለውን ወገኖቻችንን በማሰብ “ሀዘን ላይ ነን” በማለት “ጥቁር እንቁጣጣሽ” ብለው የነበራቸውን የሙዚቃ ዝግጅት ሲሰርዙ እሷ ግን አስቦ ማድረግ ቢያቅታት እንኳን በተደጋጋሚ ሙዚቃ ዝግጅቷን እንደ የሙያ አጋሮቿ እንድትሰርዝ ብትጠየቅም “እምቢ አሻፈረኝ” በማለት በወገኖቻችን ሞትና ሀዘን ላይ ስትዘፍንና ዳንኪራዋን ስትመታ አድራለች።
*የዘረኛውና የጨፍጫፊው የትግራይ ወያኔ መሪ መለስ ዜናዊ ሲሞት በህይወት ዘመኑ በወገኖቻችን ላይ የከፋ አረመኔያዊ ግፍ ሲፈጽም የነበረን ሰው ከነንዋይ ደበበ ጋር በመሆን “የሙሴ በትር” በሚል ሲፈጽም የነበረውን በደል አድንቃ በመዝፈን በወገኖቻችን ስቃይ ላይ አላግጣለች። ሙዚቃውን ከyoutube ላይ ሰምቶ ፍርድ መስጠት ይቻላል።
*ዛሬም ወገኖቻችን በመላው ኢትዮጲያ በአስቸኳይ አዋጅ ስም በተለይ በእራሷ የትውልድ ሀገር በጎንደር ይህ ነው የማይባል ግፍ በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ እሷ ግን ቀድሞ የሰራችውን በደልና ጥፋት በመርሳት ህዝብን ለፈጸመችው ስህተት ይቅርታ ሳትጠይቅ ዶላር ለመሰብሰብ በእስራኤል ሀገር በቴልአቪቭ ከተማ በፈረንጆች አቆጣጠር አርብ በ17-03-2017 የሙዚቃ ዝግጅት አዘጋጅታለች። እናም ለእሷም ለወደፊቱ የዚህ አይነት ጥፋት እንዳትደግምና እንደሙያ አጋሮቿ ከህዝቧና ከወገኖቿ ጋር እንድትቆም ትምህርት እንዲሆናት በ17-03-2017 በእስራኤል ሀገር ባዘጋጀችው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ባለመገኘት የህዝብ ወገነተኝነታችንን እናሳይ።
— በሁለት ቢላ መብላት አይቻልም ወይ ከህዝብ ወይ ከጨፍጫፊው የወያኔ ስርአት አንዱን ትምረጥ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *