“ኢንተለክቹዋል” ፕሮስቲቱሽን;- “ለፕሮፌሰር” ህዝቅኤል መስቀሉ አየለ የትኛው እስቴት እንደሆን ባላስታውስም የስፓኒሽ ቋንቋ ተናጋሪና በአሜሪካን አገር ነዋሪ የሆኑ ዜጎች እንግሊዝኛ ለምናችን አፍ መፍቻችን ጌጣችን ብለው ትምህርት በስፓኒሽ እንዲሰጣቸው የመብት ጥያቄ አቀረቡ። ይኽን የሚያደርጉት ነፍስና ስጋዋ ከእንግሊዝኛ በተሰራው አሜሪካ ተቀምጠው ነው። አገሩ ሃብታም ነው እና የትምህርት ካሬክለሙን በሃያ አራት ሰዓት ገልብጦ ሰጣቸው። ልጆቻቸውን በቋንቋቸው ማስተማር ጀመሩ። ነገር ግን ዋሽንግተን ማለት ማድሪድ ወይንም ሃቫና አይደለምና በላቲን ተምረው ምን ይዋጣቸው ?፤መዘዙ አንድ ትውልድ የስፓኒሽ ቋንቋ ተናጋሪ ሳህን አጣቢና ግምበኛ ሆኖ መቅረቱ ነበር። ዛሬ ከጥፋታቸው ተምረው እንደገና ለነፍሳቸው በስፓኒሽ ሲጸልዩ; ለፍቅራቸውም በስፓኒሽ ሲያዜሙና ሲገጥሙ እና ለደመወዛቸው ደግሞ በእንግሊዝኛ ይማራሉ። ዌልሾችም ሆኑ አይሪሾጭ የራሳቸው ቋንቋ አላቸው። ነገር ግን እንግሊዝኛ ከሰማይ በታች ያሉትን ነገር አሙዋልቶ በመግለጥ እረገድ የሰባት ሚሊዮን ቃላት ባላጸጋ በመሆኑ እንግሊዞቹን ስለጠሉ ብቻ በቋንቋችን እንማር ቢሉ የሚገጣምቸውን ያውቁታልና እነዚህ ህዝቦች ዛሬ ይኽን ቋንቋ ከእንግሊዞች እኩል ይጠቀሙበታል። የእብድ ገላጋይ ጨቤ ያቀብላል እንዲሉ በእኛ አገር እየሆነ ያለው ግን ሱሪ ባንገት አይነት ነገር ነው።ላቲኑን ከአውሮፓ አሮጌ መጋዘን አውጥተው በአበሻ ምድር ነፍስ እንድዘራ ለማድረግ የተሄደበት እብደት ነው:: የኦሮሞ ህዝብ ትግል ባለቤት ነን የሚሉት ሰዎች አማርኛን ከጠሉ በእንግሊዝኛ ቢያስተምሩዋቸው ያባት ነበር፤ የትውልዱን ሞት ሁለት ሞት የሚያደርገውም ይኸው ነው። ነገር ግን ከተወለደበት መሃል ሮምና ከቫቲካን እምብርት አርጅቶ ተገፍቶ ወጥቶ መጋዘን በተቀመጠ የላቲን ጃርገን ይማሩ ብሎ የትውልድን መጻኢ እድል መወሰን ማለት ምን እንደሆነ የወያኔ ግልጥ ሲሆን የኦነጎቹን ትክክለኛ ደዌ ግን የሚያዉቁት እራሳቸው የኦነግ ጥራዝ ነጠቆች ናቸው። የአገሪቱ ጅዲፒ ስልሳ አምስት በመቶው አዲስ አበባ እነ ወለጋና ኤሊባቡር ግን የበሬውን ጭራ በሆኑበት አገር አማርኛ የማይናገርና ከመሃል ሸዋ እምብርት ተቆርጦ የተጣለ ትውልድ መፍጠር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማሰብ እንደነሱ በሽተኛ መሆንን ይጠይቃል። ሌላው ጉዳዩን ይበልጥ ውስብስብ የሚያደርገው ነገር ዛሬ በአማርኛ አስከሬን ላይ የቁቤ ጀነሬሽን እንፈጥራለን ብለው ሌት ተቀን በህወሃት ማሊያ ለኦነግ የሚጫወቱት የኦህዴድ ባለልጣናት ከህዝቡ በሚዘርፉት ገንዘብ ልጆቻቸውን አዲስ አበባ ልከው ሲያስተምሩ የመርዘኛ ፖሊስያቸው ሰለባ እየሆነ ያለው ግን የእንጨት ለቃሚዋ ልጅ የመሆኑ ነገር ነው። የዚህን ፓሊሲ ውድቀት ለማየት እሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ ሁለት ቦታ ማየት ብቻ በቂ ነው። ፩ አዲስ አበባ ሚግሬሽን ተሰልፈው ፓስፖርት ሊያወጡ ከኦሮሚያ የሚመጡ ወጣቶችን የፓስፖርት መጠየቂያ ቅጽ ሙሉልን እያሉ ሰው ሲለምኑ ማየት ምን ያህል ቅስም ሰባሪ እንደ ሆነ ፪ በትውልድ አማራ ለሆኑት ተብላ የተፈቀደችና ትምህርት በአማርኛ የሚሰጥባት በወሊሶ ከተማ አንዲት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አለች። ባለባት የቦታ ጥበት የተነሳ መቀበል የምትችለው በጣም ውሱን የሆነ ተማሪ በመሆኑ ልጆቻቸውን እዚህች ትምህርት ቤት አስገብተው ለማስተማር ሁለት ሶስት አመት ሙሉ በእምብርክክ እየሄዱ ደጅ የሚጠኑትን የኦሮሞ ቤተሰቦች ሃዘን መስፈር የሚቻልበት ሚዛን እንዳለ አላውቅም።ልብ ሰባሪ ነው። ልጆቹ የኦሮሞኛን ጨምሮ ማናቸውንም ቋንቋ እንዲያውቁ ማድረግ፣ባህሉን ወጉን ማሳደግ እኛም ደስ ብሎን በአኮቴት የምንግራው ነገር ነው። አማርኛን እዳያውቁ ማድረግ ደግሞ ሌላ ነገር ነው። በአንጻሩ አንድ በቅርብ የማውቀው ሰው እንደነገርኝ በሜኔሶታ ያሉ አንዳንድ ሬስቶራንቶች የምግብ ማውጫ ዝርዝራቸው (ሜኖ) የተጻፈው በቁቤ በመሆኑ አማርኛ ለሚናገር ሰው ግልጋሎት አይሰጡም ማለት ነው። እንዲህ ተሁኖ የሚነገደው የገንዘብ ጭራቃዊ ገጽታ በቁመተ ስጋ በሚታይባት አሜሪካ እየተኖረ መሆኑ እንቆቅልሹን አስገራሚ ያደርገዋል። አንድ በደቡብ ክልል ነዋሪ የሆኑ አዛውንት ለመለስ ዜናዊ በላኩት መልእክት አንተ ልጆች ህን በእንግሊዝኛ እያስተማርክ የኛን ልጆች ግን በአማርኛ የመማር መብት ስትጨፈልቅ ለኛ የገባን ነገር ልጆቻችንን በወጋጎዳ ተማሩ በሚል ሽፋን እዚሁ ሸማኔ ሆነው ወንዝ እንዳይሻገሩ ከማድረግ የዘለለ እኩይ አላማ እንዳላነገባችሁ ነው ማለታቸው ይጠቀሳል። ይኽ ሰው ይኽን የተናገሩት የተባለው የአዋሳ ህዝብ ልጆቹ ወያኔ ሰራሽ በሆነውና ከአራት ቋንቋ ተጨፍልቆ በተሳራው ወጋጎዳ የተጻፈ የትምህርት ካሬክለም በሁለት መቶ ሚልዮን ብር ታትሞ በአዋሳ ከተማ እንደደረሰ መጻህፍቶቹ ከመሰራጨታቸው በፊት ለማቃጠል የወሰደውን እርምጃ ለመቀልበስ በረከት ስሞን በመራው ዘመቻ በከሶስት መቶ ያላነሱ ንጹሃን ዜጎች ያለቁበትን ትራጀዲ ተከትሎ ነበር። አማርኛ የማይሰማ ትውልድ መፍጠር በርግጥም ስኬት ነው ከተባለ በህዝቅያስና በሳሞራ የኑስ “ፕሮፌስርነት” መካከል ምንም ልዩነት የለም ማለት ነው።

“ኢንተለክቹዋል” ፕሮስቲቱሽን;- “ለፕሮፌሰር” ህዝቅኤል17e131a
መስቀሉ አየለ
የትኛው እስቴት እንደሆን ባላስታውስም የስፓኒሽ ቋንቋ ተናጋሪና በአሜሪካን አገር ነዋሪ የሆኑ ዜጎች እንግሊዝኛ ለምናችን አፍ መፍቻችን ጌጣችን ብለው ትምህርት በስፓኒሽ እንዲሰጣቸው የመብት ጥያቄ አቀረቡ። ይኽን የሚያደርጉት ነፍስና ስጋዋ ከእንግሊዝኛ በተሰራው አሜሪካ ተቀምጠው ነው። አገሩ ሃብታም ነው እና የትምህርት ካሬክለሙን በሃያ አራት ሰዓት ገልብጦ ሰጣቸው። ልጆቻቸውን በቋንቋቸው ማስተማር ጀመሩ። ነገር ግን ዋሽንግተን ማለት ማድሪድ ወይንም ሃቫና አይደለምና በላቲን ተምረው ምን ይዋጣቸው ?፤መዘዙ አንድ ትውልድ የስፓኒሽ ቋንቋ ተናጋሪ ሳህን አጣቢና ግምበኛ ሆኖ መቅረቱ ነበር። ዛሬ ከጥፋታቸው ተምረው እንደገና ለነፍሳቸው በስፓኒሽ ሲጸልዩ; ለፍቅራቸውም በስፓኒሽ ሲያዜሙና ሲገጥሙ እና ለደመወዛቸው ደግሞ በእንግሊዝኛ ይማራሉ።
ዌልሾችም ሆኑ አይሪሾጭ የራሳቸው ቋንቋ አላቸው። ነገር ግን እንግሊዝኛ ከሰማይ በታች ያሉትን ነገር አሙዋልቶ በመግለጥ እረገድ የሰባት ሚሊዮን ቃላት ባላጸጋ በመሆኑ እንግሊዞቹን ስለጠሉ ብቻ በቋንቋችን እንማር ቢሉ የሚገጣምቸውን ያውቁታልና እነዚህ ህዝቦች ዛሬ ይኽን ቋንቋ ከእንግሊዞች እኩል ይጠቀሙበታል።
የእብድ ገላጋይ ጨቤ ያቀብላል እንዲሉ በእኛ አገር እየሆነ ያለው ግን ሱሪ ባንገት አይነት ነገር ነው።ላቲኑን ከአውሮፓ አሮጌ መጋዘን አውጥተው በአበሻ ምድር ነፍስ እንድዘራ ለማድረግ የተሄደበት እብደት ነው:: የኦሮሞ ህዝብ ትግል ባለቤት ነን የሚሉት ሰዎች አማርኛን ከጠሉ በእንግሊዝኛ ቢያስተምሩዋቸው ያባት ነበር፤ የትውልዱን ሞት ሁለት ሞት የሚያደርገውም ይኸው ነው። ነገር ግን ከተወለደበት መሃል ሮምና ከቫቲካን እምብርት አርጅቶ ተገፍቶ ወጥቶ መጋዘን በተቀመጠ የላቲን ጃርገን ይማሩ ብሎ የትውልድን መጻኢ እድል መወሰን ማለት ምን እንደሆነ የወያኔ ግልጥ ሲሆን የኦነጎቹን ትክክለኛ ደዌ ግን የሚያዉቁት እራሳቸው የኦነግ ጥራዝ ነጠቆች ናቸው። የአገሪቱ ጅዲፒ ስልሳ አምስት በመቶው አዲስ አበባ እነ ወለጋና ኤሊባቡር ግን የበሬውን ጭራ በሆኑበት አገር አማርኛ የማይናገርና ከመሃል ሸዋ እምብርት ተቆርጦ የተጣለ ትውልድ መፍጠር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማሰብ እንደነሱ በሽተኛ መሆንን ይጠይቃል።
ሌላው ጉዳዩን ይበልጥ ውስብስብ የሚያደርገው ነገር ዛሬ በአማርኛ አስከሬን ላይ የቁቤ ጀነሬሽን እንፈጥራለን ብለው ሌት ተቀን በህወሃት ማሊያ ለኦነግ የሚጫወቱት የኦህዴድ ባለልጣናት ከህዝቡ በሚዘርፉት ገንዘብ ልጆቻቸውን አዲስ አበባ ልከው ሲያስተምሩ የመርዘኛ ፖሊስያቸው ሰለባ እየሆነ ያለው ግን የእንጨት ለቃሚዋ ልጅ የመሆኑ ነገር ነው።
የዚህን ፓሊሲ ውድቀት ለማየት እሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ ሁለት ቦታ ማየት ብቻ በቂ ነው።
፩ አዲስ አበባ ሚግሬሽን ተሰልፈው ፓስፖርት ሊያወጡ ከኦሮሚያ የሚመጡ ወጣቶችን የፓስፖርት መጠየቂያ ቅጽ ሙሉልን እያሉ ሰው ሲለምኑ ማየት ምን ያህል ቅስም ሰባሪ እንደ ሆነ
፪ በትውልድ አማራ ለሆኑት ተብላ የተፈቀደችና ትምህርት በአማርኛ የሚሰጥባት በወሊሶ ከተማ አንዲት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አለች። ባለባት የቦታ ጥበት የተነሳ መቀበል የምትችለው በጣም ውሱን የሆነ ተማሪ በመሆኑ ልጆቻቸውን እዚህች ትምህርት ቤት አስገብተው ለማስተማር ሁለት ሶስት አመት ሙሉ በእምብርክክ እየሄዱ ደጅ የሚጠኑትን የኦሮሞ ቤተሰቦች ሃዘን መስፈር የሚቻልበት ሚዛን እንዳለ አላውቅም።ልብ ሰባሪ ነው። ልጆቹ የኦሮሞኛን ጨምሮ ማናቸውንም ቋንቋ እንዲያውቁ ማድረግ፣ባህሉን ወጉን ማሳደግ እኛም ደስ ብሎን በአኮቴት የምንግራው ነገር ነው። አማርኛን እዳያውቁ ማድረግ ደግሞ ሌላ ነገር ነው።
በአንጻሩ አንድ በቅርብ የማውቀው ሰው እንደነገርኝ በሜኔሶታ ያሉ አንዳንድ ሬስቶራንቶች የምግብ ማውጫ ዝርዝራቸው (ሜኖ) የተጻፈው በቁቤ በመሆኑ አማርኛ ለሚናገር ሰው ግልጋሎት አይሰጡም ማለት ነው። እንዲህ ተሁኖ የሚነገደው የገንዘብ ጭራቃዊ ገጽታ በቁመተ ስጋ በሚታይባት አሜሪካ እየተኖረ መሆኑ እንቆቅልሹን አስገራሚ ያደርገዋል። አንድ በደቡብ ክልል ነዋሪ የሆኑ አዛውንት ለመለስ ዜናዊ በላኩት መልእክት አንተ ልጆች ህን በእንግሊዝኛ እያስተማርክ የኛን ልጆች ግን በአማርኛ የመማር መብት ስትጨፈልቅ ለኛ የገባን ነገር ልጆቻችንን በወጋጎዳ ተማሩ በሚል ሽፋን እዚሁ ሸማኔ ሆነው ወንዝ እንዳይሻገሩ ከማድረግ የዘለለ እኩይ አላማ እንዳላነገባችሁ ነው ማለታቸው ይጠቀሳል። ይኽ ሰው ይኽን የተናገሩት የተባለው የአዋሳ ህዝብ ልጆቹ ወያኔ ሰራሽ በሆነውና ከአራት ቋንቋ ተጨፍልቆ በተሳራው ወጋጎዳ የተጻፈ የትምህርት ካሬክለም በሁለት መቶ ሚልዮን ብር ታትሞ በአዋሳ ከተማ እንደደረሰ መጻህፍቶቹ ከመሰራጨታቸው በፊት ለማቃጠል የወሰደውን እርምጃ ለመቀልበስ በረከት ስሞን በመራው ዘመቻ በከሶስት መቶ ያላነሱ ንጹሃን ዜጎች ያለቁበትን ትራጀዲ ተከትሎ ነበር። አማርኛ የማይሰማ ትውልድ መፍጠር በርግጥም ስኬት ነው ከተባለ በህዝቅያስና በሳሞራ የኑስ “ፕሮፌስርነት” መካከል ምንም ልዩነት የለም ማለት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *