የህውሃት ወታደሮችን የጫነ የጦር ተሽከርካሪ በመራቤቴ በጥይት ተመቶ ተገለበጠ። አገዛዙ ዳግም ወታደሮችን በሞት ተነጥቋል

በዘርይሁን ሹመቴ

ካአገዛዙ ፈትልከው የሚወጡ ወታደራዊ መረጃዎች በጎንደር በየተራራውና በየጫካው ሸምቀው በሚፋለሙ አማሮች እጅ እየገባ አገዛዙን ለተደጋጋሚ ሽንፈት እየዳረጉት እንደሚገኙ ታወቀ።ethiopian-soldiers

ወያኔ በሚስጥር ያቀዳቸው ወታደራዊ ተልእኮዎች አገዛዙን በጠመንጃ አፈ ሙዝ እየተጋፈጡት ላሉ ለአማራ አርበኞች ቀድሞ እንደሚደርሳቸው ባሳለፍነው ሳምንት በሸዋ መራቤቴ ተፈጸመ የተባለው ክስተት ማመሳከሪያ ይሆናል ተባለ።

በጥር 7 ቀን 2009ዓም በሽምቅ በሚታገሉት አማሮች ላይ ወታደራዊ ተልእኮ እንዲወጡ በሸዋ መራቢቴ ወደ ሚገኝ ተራራ የተላኩ የወያኔ ወታደሮች ያልጠበቁት ጥቃት እንደተሰነዘረባቸው ተሰምቷል።

በደናማው ተራራ ሸምቀው ከአገዛዙ ጋር የትጥቅ ትግል የገጠሙት አርበኞች ቀድሞ በደረሳቸው መረጃ የወያኔን ወታደሮች ጭኖ ወደ ቦታው እያመራ ባለ የጦር ተሽከርካሪ ላይ በከፈቱት ድንገተኛ ጥቃት ተሽከርካሪው መገልበጡ ታውቋል።

በጦር ተሽከርካሪው ላይ ተጭነው ከነበሩ የህውሃት ወታደሮች ውስጥ ሶስቱ (3) ወዲያውኑ መሞታቸውን እንዳረጋገጠ የአማራ ድምጽ ዘግቧል።

ይህ የጦር ተሽከርካሪ በአማራ ተጋዳዮች በተተኮሰበት ጥይት የፊት ጎማዎቹ በመፈንዳታቸው ወታደሮቹን እንደጫነ ተገልብጦል።

በዚህም ጥቃት የግድያ ተልእኮ እንዲወጡ የተላኩት የወያኔ ወታደሮች ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተሰምቷል ።

እንደነዚህ አይነቶች ጥብቅ ወታደራዊ ሚስጥሮች ለነጻነት እየተጋደሉ ባሉ የአማራ አርበኞች እጅ በተደጋጋሚ ቀድሞ መድረስ በርግጥም ወያኔ በአማራ ክልል አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ መግባቱን ያሳያል።

አገዛዙ በሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ወታደር ቢያሰፍርም ከአስደንጋጭና ካልተጠበቀ ሽንፈት አሁንም መዳን እንዳልቻለ እየታየ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *