ጋምቤላ ልጆቿ በጥይት የተጨፈጨፉበት ምክንያት ይፋ ሆነ! የካሩቱሪ መሬት ለትግራይ “ባለሃብቶች” ሊሰጥ ነው

ጋምቤላ ልጆቿ በጥይት የተጨፈጨፉበት ምክንያት ይፋ ሆነ!

የካሩቱሪ መሬት ለትግራይ “ባለሃብቶች” ሊሰጥ ነው

ዜናውን “መገጣጠም” ሲሉ በቁጭት ይገልጹታል። የትግራይ “ባለሃብቶች” በጋምቤላ መበደላቸውን ለውጭ አገርና ለአገር ውስጥ መገናኛዎች ያስታወቁበት ዕለትና የአኙዋክ ምስኪኖች በምድራቸው በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን ተሳሳመ።

ደም እንደጎርፈ በፈሰሰበት፣ ንጹሃን እንደ እንስሳ የተቀሉብት ቀን ተዘንግቶ በሙታን ዱካ ተተክተው “ተበደልን” ያሉ የብሶት ዜና ተሰማበት – ታህሳስ 4፤ 2009 (ዲሴምበር 13 ቀን 2016)።fb_img_1481950935552

ታህሳስ 3፤ 1996 ዓ.ም በጋምቤላ ለተጨፈጨፉት ንጹሃኖች ፍትህና ርትዕ የሚሰጥ አካል እስካሁን አልተገኘም። በስደት ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና የተለያዩ አገራት የሚኖሩ የአኙዋክ ተወላጆች ያንን ቀን ሲያስቡት አሁን ድረስ ያነባሉ። በመለስ አመራር ሌሎች በፌዴራል መንግሥት ስም የሚታወቁ የህወሃት ሰዎች ትዕዛዝ ከ400 በላይ አኙዋኮች ተረሽነዋል። አሁን እነሱ አፈር ውስጥ ሆነው ደማቸው ከላይ ይጮሃል።

በእነሱ ደምና አጽም ላይ ንግድ ጦፏል።
ከያቅጣጫው ከተፈጥሮ ዛፎቿ ጀምሮ ጋምቤላ እየታለበች ነው። ካሩቱሪ፣ ሳውዲ ስታር እና 1000 የሚሆኑ የትግራይ “ባለሃብቶች” /ነባር ታጋዮች ናቸው/ በዚሁ የደም መሬት ላይ ሰፍረው ይበደራሉ፣ የክልሉን ህዝብ ጭሰኛ አድርገው ያመርታሉ፣ ይነግዳሉ፣ ይለውጣሉ፣ …
ታህሳስ 4፤ 2009 (ዲሴምበር 13 ቀን 2016) የቪኦኤ የትግራይ ዘጋቢ “የጋምቤላ እርሻ ባለሐብቶች የሕብረት ሥራ ማኅበር” በሚል ስያሜ የሚጠራውን የቀድሞ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ታጋዮች “በደል” ይፋ አድርጓል። የማህበሩን ሊቀ መንበር አቶ የማነ ሰይፉን አነጋግሯል።

ማህበሩ ያሰማው ቅሬታ የትግራይ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ በደል እንደደረሰባቸው ነው። አንድ ሺህ የሚሆኑት የትግራይ ባለሃብቶች ያመረቱት ማሳ ላይ እያለ ብድር መከልከላቸው ሆን ተብሎ የተደረገና በማንነታቸው የደረሰባቸው በደል ነው። ከ2001 ጀምሮ ወደ ጋምቤላ ባለሃብት ሆነው የገቡት የትግራይ ተወላጆች፣ የባንክ ብድር ማግኘት የጀመሩት ከ2005 ጀምሮ ሲሆን በያዝነው ዓመት ተቋርጦባቸዋል። ይህም የሆነው እነሱን አክስሮ ከጫወታ ውጪ ለማስገባት ነው ብለዋል።

ቀደም ሲል በሄክታር 30 ብር ግብር ይከፍሉ ነበር አሁን በቅጽበት ወደ 111 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል። የባንክ ብድር ወለድም ከ8.5 ወደ 12.5 ከፍ እንደተደረገባቸው ያስረዱት ሊቀመንበሩ፣ ደጋግመው የተናገሩት ድርጊቱ ሆን ተብሎ እነሱ ላይ በተነጣጠረ ሴራ መሆኑን ነው።

ጋምቤላ ልጆቿ በጥይት የተጨፈጨፉበት ምክንያት ይፋ ሆነ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *