በዘመኔ ፋሽስቶቹ ወያኔዎች ለመከራ በተፈጠረው የኔ ዘመን የአማራ ትውልድ ላይ የፈጽሙትን ጭካኔ ቆሞ ሲሄድ በአይኔ አይቸዋለሁ።

ተነግሮ የማያልቀው የአማራ ግፍና በደል [ክፍል ፩]

በዘመኔ ፋሽስቶቹ ወያኔዎች ለመከራ በተፈጠረው የኔ ዘመን የአማራ ትውልድ ላይ የፈጽሙትን ጭካኔ ቆሞ ሲሄድ በአይኔ አይቸዋለሁ። በ1998 ዓ.ም. አማራ በመሆናቸው ብቻ አገር ሰላም ብለው ዶርማቸው ተቀምጠው ሳለ የትግራይ ወታደሮች በርግደው በመግባት ጭንቅላታቸውን በጥይት አፍርሰው የጣሏቸውን ከጥይት የተረፉ የአማራ ተማሪዎች መቀሌ ሆስፒታል ልናሳክም ወስደናቸው አማራ መሆናቸው በመታወቂያቸው ሲታወቅ «ቅንጅት ያክማቸው» ተብለው ህክምና ሳያገኙ ደማቸው በልብሳቸው ፈሶ አልቆ በክንዳችን ላይ እንዲሞቱ የተደረጉ የአማራ ገበሬ ልጆችን አውቃለሁ። ኸረ ስንቱ ተነግሮ ያልቃል! ፋሽስቶቹ የትግራይ ወታደሮች በአማራ ላይ እየፈጸሙት ያለው ግፍና ሰቆቃ ምድሪቷ ከምትሸከመው በላይ ሆኗል።

ከታች የታተመው የኦሮሞ ልጅ ያየውን የአማራ ግፍ ይናገራል። እንዲህ ግፋችን እየተመዘገበ፤ በደላችን ከቁጥር እየገባ ሲከማች፤ ዛሬ ለናንተ ያደላው ወረተኛው ጊዜ ነገ ወደ ግፉዓን ዘንበል ሲል፤ ለናንተ የማለዳ ጸሀይ የሆነው የኛ ጨለማ፤ ለናንተ የወፎች ዜማ የሆነው የኛ ሰቅሶ ፍርድ ማግኝቱ አይቀርም። ይህ ጊዜ ይመጣ ዘንድ በግፍ የወደቁት የአማራ ልጆች ደም ዛሬም አፍ አውጥቶ እየጮኸ ነው። የፍትህ ያለህ! የእውነት ያለህ! የፈጣሬ ያለህ! እያለ ነው።

ታላቁ ሊቅ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ከ42 ዓመታት በፊት «ኸረ ስማ እግዚአብሔር!» በማለት ዘመን በማይሽረው ግጥማቸው «እንጉርጉሮ» ሲሉ ባሳተሙት የግጥም መድበላቸው ውስጥ ከአጼው መውደቅ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ስለቆየብን ግፍና ሰቆቃ የታያቸው ይመስስል ፈጣሬያቸውን ስማኝ ባክህን ሲሉ ተማጽነው ነበር። . . . .!

እኔም እጣራለሁ. . . . «ኸረ ስማ እግዚአብሔር!». . . እላለሁ. . .
_______________
ኸረ ስማ እግዚአብሔር!

ኸረ ስማ እግዚአብሔር !
ተቸገረ ፍጡር!
እስከመቼ ድረስ ዝም ብለህ ታያለህ?
አይሰለችህም ወይ አቤት! አቤት! ቢሉህ?
ቸግሮህ ይሆን ወይ? ብልሃቱ ጠፍቶብህ፤
ባንተው እጅ ስራ በገዛ ትንፋሽህ፤
አንተ እኛን ፈጠርከን፤
እኛ ተንኮል ፈጠርን፤
ተጎልተን ቀረን፤
እንዲሁ ተፋጠን!
ኸረ ስማ እግዚአብሔር!
ተጨነቀ ፍጡር!
ትካዜ፤ ድንጋጤ፤ ጸጸት ገባህ እንዴ?
አንተው በሰራኸው ባዋቂው ወንበዴ?
ተናደህ ይሆን ወይ? በታመመው ዓለም፤
ፍርድህን ወስነህ ልታጠፋው ፍጹም?
ምነው እንዲህ ዝም አልክ?
እሺ ነገን ተማርከው!
ርቀት ነው ንቀት?
ጭካኔ ነው ፍርሃት?
ኸረ ስማ እግዚአብሔር!
ተቸገረ ፍጡር!
ስራ በዝቶብህ ነው? ወይንስ ረስተኸን?
ቴያትር እያየህ ትስቅብን ይሆን?
ጻድቃን፤ መላእክቱ፤ ምን ምክር ያቀርባሉ?
አያማልዱም ወይ ስለት እየበሉ?
ኃይለኞች ምን አሉህ?
ሀብታሞች ምን ሰጡህ?
እንደዚህ ጭጭ ያልከው!
ወይ እንኳ እማትለው?
ኸረ ስማ እግዚአብሔር!
ተሸበረ ፍጡር!
በስምንተኛው ሺህ ቴክኒኩ ሲሻሻል፤
ስልኩ ጸሎታችን እንዴት ይበላሻል?
ለውጠህም እንደሁ የስልክህን ቁጥር፤
ላክልን ልጅህን ዳግም እንዲያስተምር።
እኛኮ ተስፋ አለን፤
ትሰማለህ ብለን።
ኸረ ስማ እግዚአብሔር!
ተቸገረ ፍጡር።
[ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም፡ 1967] ከአቻሜለክ ታምሩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *