ጠላትህን እወቅ !!

ጠላትህን እወቅ!
የነጻነት ትግል እንደ ልፍያ ቀላል አይደለም። ትግሉ የህይወት ዋጋ ያስከፍላል፣ አካለ ጎደሎ፣ እስረኛ፣ የአልጋ ቁራኛ ስደተኛ እና ግዦተኛ ያደርጋል። እኛ ተበዳዮቹ በዳቢሎስ መንፈስ ተሞልተው ዜግነታዊ መብታችንን፣ ሰብአዊ ክብራችንን፣ ታሪካችንን በአጠቃላይ ሰብአዊ ማንነታችንን ሁሉ የገፈፉንን ጠላቶቻችንን ለይተን እንወቅ። ለኢትዮጵያ ህዝብ ዋነኛው ጠላት ወያኔ ነው። ከነሱ የከፋ ጠላት በታሪካችን ገጥሞን አያውቅም።
ስለዚህም ከልቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት አስተዋጽኦ ለማድረግ የተነሳ ሁሉ ጊዜውን በከንቱ አያጥፋ። መቀመቅ ውስጥ ገብተን በተራ ንትርክ የምናጠፋው ጊዜና ጉልበት ሊያሳዝነን ይገባል። ስለዚህንም በፌስቡክም ይሁን በሌሎች መድረኮች ላይ በሚደረግ ተራ ንትርክ እና የቃላት ልውውጥ ከመሳተፍ እንቆጠብ። fb_img_1480803434022
ሁላችንም ከፊታችን ያለውን ፈታኝ እና መራራ ትግል እያሰብን ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ሲሉ መተኪያ የሌላት ህይወታቸውን የገብሩትን መከራና ስቃይ በጸጋ የተቀበሉትን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን፣ ክብራቸውንና የግል ህይወታቸውን ትተው መሬት ላይ የወረዱትን መሪዎቻችንን ዘወትር እያሰብን ትግላችንን በጽናት እንቀጥል። አላማችንን እንዳንስት ዋነኛ ትኩረታችን ጠላቶቻችን ላይ ብቻ ይሁን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *