የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔ ጦር ላይ በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን በመቀጠል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታወቀ፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
*****************
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔ ጦር ላይ በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን በመቀጠል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታወቀ፡፡
*****************
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ነበልባል የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም ለሊት ጎንደር ዳንሻ ከተማ ልዩ ስሙ አዲስ አለም በተባለ ቦታ ሰፍሮ ከሚገኝ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው ድንገተኛ ማጥቃት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ አጥቅቶ ተሰውሯል፡፡ በወሰደው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃም 15 የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮችን በመግደል ቁጥራቸው ያልታወቀ ደግሞ ማቁሰሉን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራው ባደረሰን ዘገባ አስታውቋል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጥቃቱን በመቀጠል ህዳር 13 ቀን 2009 ዓ.ም በአብደራፊ ከተማ ዙሪያ በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ላይ ተመሳሳይ የደፈጣ ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን ባደረገው ሰፊ የማጥቃት እርምጃም 25 በመግደልና 17 በማቁሰል በቅጥረኛው የህወሓት ጦር ላይ ጠንካራ ክንዱን በማሳረፍ የበላይነትን ተጎናፅፎ የህወሓት ቅጥረኛ ወታደሮችን እንቅስቃሴ በመግታት መበታተን እንደቻለ ሪፖረተራችን አክሎ ገልጿል፡፡fb_img_1479641031143
ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እየፈፀመ ያለውን ቆራጥ ተጋድሎ ጥቃቱ በሚፈፀምበት ቦታ ሁሉ ሙሉ በሙሉ የህዝብን ድጋፍ እያገኘ ሲሆን የቆመለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ትልቅ ጉልበት እንደሆነው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እስኪሆን ድረስም ጀግኖች የአርበኞች ግንቦት 7 ነበልባል ሰራዊት ወደፊት በመግፋት በተግባር የኢትዮጵያ አለኝታነታቸውን እያስመሰከሩ ይገኛሉ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *