ዛሬ በአርማጭሆና በጠገዴ አካባቢዎች በዋለው ጦርነት ከ70 በላይ የወያኔ ወታደሮች በዐማራ ታጋዮች ተደምስሰዋል፤

ከ70 በላይ የወያኔ ወታደሮች ተገድለዋል፤ ሁለት የወገን አርበኞች ተሰውተዋል
በጎንደር ዩንቨርሲቲ የዐማራ ተወላጅ ተማሪዎች በገፍ እታሰሩ ነው፤

ዛሬ በአርማጭሆና በጠገዴ አካባቢዎች በዋለው ጦርነት ከ70 በላይ የወያኔ ወታደሮች በዐማራ ታጋዮች ተደምስሰዋል፤ በርካታ ቀላልና ከባድ የጦር መሣሪዎችም ተማርከዋል፡፡ ከከፋኝ የዐማራ ታጋዮች በኩል ሁለት አርበኞች መሰዋታቸውን ከመሸ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡
አርበኛ ሞላ አጃው የተባለ በ2008 ዓ.ም. በጎንደር ባዕታ አካባቢ ከነበረው ማረሚያ ቤት ቃጠሎ በተነሳበት ወቅት ከወያኔ እስር አምልጦ በአርማጭሆና በጠገዴ አካባቢ ከወያኔ ጦር ጋር ጀብድ ሲሠራ የቆየው ታላቅ አርበኛ ዛሬ በነበረው ውጊያ መስዋት መሆኑ ታውቋል፡፡ አቶ ሞላ አጃው ከወልቃይት ጠገዴ የዐማራ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በሕወሓት ታስሮ ከቆየ በኋላ በጀግንነት ከወያኔ እስር አምልጦ ነበር፡፡ ከማረሚያ ቤት ከወጣ በኋላ በርካታ የጦር ሜዳ ጀብዱዎችን ፈጽሟል፡፡ አርበኛ ሞላ አጃው ዛሬ ኅዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ከጠላት ጋር ተናንቆ ለወገኑ ሲል ተሰውቷል፡፡ ከአርበኛ ሞላ አጃው ጋር ለጊዜው ስሙን ያላወቅነው የዐማራ አርበኛም ተሰውቷል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በጎንደር ዩኝቨርሲቲ ቁጥራቸው ያልታወቁ ተማሪዎች በሦስት መኪናዎች በወታደር ተጭነው መወሳዳቸው ታውቋል፡፡ ተማሪዎቹን የአጋዚ ወታደሮች የወሰዱበት ቦታ ያልታወቀ ሲሆን ዩንቨርሲቲው አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት መኖሩም ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *