እዚህ ፌስ ቡክና ሌላም ሶሻል ሚዲያ ላይ የአማራ ተቆርቋሪ ነን ፣ የአማራ ድርጅት ነን ፣ ጎንደር ውስጥ ያለው የትጥቅ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ነን የሚሉ ሰዎችን……ከፈቃደ ሸዋ ቀና

እዚህ ፌስ ቡክና ሌላም ሶሻል ሚዲያ ላይ የአማራ ተቆርቋሪ ነን ፣ የአማራ ድርጅት ነን ፣ ጎንደር ውስጥ ያለው የትጥቅ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ነን የሚሉ ሰዎችን ብዙዎቹ በዚያው አፋቸው የኤርትራን መንግስት እንደጠላት እንደሚቆጥሩና እየዘለፉ ሲናገሩ ስሰማ ፖለቲካቸውን እያሰቡ መስራታቸውን እጠራጠራለሁ። በተለይ ስለትጥቅ ትግሉ መንገድና መድረሻ ስትራቴጂክ ሁሳብ ማሰብ እንዳለባቸውና አዛላቂ ራዕይ መያዝ እንደሚያስፈልጋቸው ያወቁ አይመስሉም።
ጎንደር ውስጥ ያሉ የአማራ የትጥቅ ተጋዳዮች ገና ብዙ አቅም ያላወጡና ብዙ የሚጠብቃቸው ናቸው። የሚታገሉት መንግስትን የሚያህል ነገር ከሚያዘው ግዙፍ ሰራዊት ጋር ነው። ያላቸውን የመሳሪያና ስንቅ አይነት ስንገምት ብዙ አውሎ የሚያሳድር አይደለም። የመሳሪያም ሆነ የስንቅ supply ለማስገባት እረዳለሁ የሚለውና ባማራነት ተደራጅቻለሁ የሚለው ሶሻል ሚዲያ ላይ የምናየው ሀይል ለዚህ የሚተባበር የጎረቤት አገር መንግስት ያስፈልገዋል። ተዋጊዎች ማፈግፈግ ሲገደዱ የሚቀበልና አንገት ይዞ የማይሰጥ የጎረቤት አገር መንግስትም ማግኘት ጥሩ ነው። የቆሰሉም መታከሚያ ቢያገኙ ጥሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ከኤርትራ የተሻለ ጎረቤት የለም። ሱዳን የማይሞከር ነው። ቢያንስ የስካሁኑ ተመክሮዋችን ይህን ነው የሚያሳየው። መሳሪያም መግባት ካለበት ከኤርትራ የተሻለ መንገድ የለም። በደፈናው የኤርትራ መንግስት አማራ አይወድም የሚል የጠንቋይ ፖለቲካ የሚጠቅም አይመስለኝም። ሻቢያ ዋና ጠላቱ ወያኔ መሆኑን ከነባራዊ እውነታው መወቅ ይቻላል። ሻቢያ ትልቁ ጉዳዩ ያለው ወያኔ መውደቅ ላይ መሆኑን ለማወቅ ሊቅ መሆን አይጠይቅም። ሻቢያ ያማራ ጠላት አለመሆኑን የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎችም አሉ። ስለሻቢያ ብዙ ያማይመረመሩ ቅቡሎች (myths) እንደውነት የተወሰዱ አሉ። ለምሳሌ ሻቢያ ኢትዮጵያ በብሄረሰብ እንድትከፋፈል ሀሳብ እመንጭቷል ፍላጎቱም ነበር ሲባል ነበር። አሁን ከብዙ ምንጮች ከወያኔዎች ጨምሮ ይህ የሻቢያ ፍላጎት እንዳልነበረ ማወቅ ችለናል። ችግር እንኩዋን ቢኖር ማለስለስ ነው የሚሻለው። ጦርነት የጦር ሜዳ ስራ ብቻ አይደለም። ይቺን እንኩዋን ማሰብ የማይችል የታጋዮቹ ደጋፊ ነኝ ባይ ምን እያሰበ እንደሚደግፍ ይገርመኛል። ትላንት ማታ ባጋጣሚ ቤት ቁጭ ብዬ ፓልቶክ ላይ ያለ ውይይት ስሰማ የአማራ ሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጃለሁ የሚለው ደምስ በለጠ ኢሳያስ አማራ ስለሚጠላ እይቻለ አማርኛ አይናገርም የሚል የጠንቋይ ፖለቲካ ሲናገር ሰምቼው ሳቅኩኝ። ልብ በሉ ሬዲዮ ይዞ የትግሉን ደጋፊዎች የፕሮፓጋንዳ ስራ የሚሰራ ሰው ነው ይህን የሚለው።ሌላም ሶሻል ሚዲያ ላይ የማያቸው የጎንደሩ ትጥቅ ትግል ደጋፊዎች ነን ባዮች ሻቢያን ሲያጥላሉና ሲከሱ መስማት ያልተለመደ አይደለም።
እንዳንድ የአማራው ህዝብ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ብሶት ማውራት ብቻ የትግል ስትራቴጂ የሚመስላቸው ሆነው አያቸዋለሁ። ብልሀት ማሰብም ትልቁ የትግሉ አካል ነው። አማራው ተገደለ፣ ተዋረደ፣ ተጨፈጨፈ በሀገሩ ባይተዋር ተደረገ የሚሉት ነገሮች ከሀያ አምስት አመት በኋላ ሰሞኑን የተገለጡላቸው የሚመስሉ ሰዎች እያየሁ ነው። ብሶት ማውራት ስትራቴጂ ወይም ራዕይ አይደለም። ለሱ ምትክ ሆኖም አይሰራም።
አንዳንዶቹ በባዶ ሜዳ ማቅራራት የሚወዱና potential የትግሉ አጋዦች ላይ የጠላትነት ፕሮፓጋንዳ ሲያካሂዱ አያለሁ። ከኢሳትና ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር የሚያጣላቸው ነገር ለምሳሌ አይገባኝም። በዚህ መንገድ ለአማሮቹ እንቅሳቃሴ ከሚያደርጉት ድጋፍ የበለጠ የሚጎዱት ነገር የሚበልጥ ይመስለኛል። እንዴህ አይነት ትግል ሰከን ብሎ ተጨንቆ ማሰብንና ዘዴና ስትራቴጂ መንደፍን፣ ትዕግስትና አስተዋይነትን ይጠይቃል። ትግሉ ጅምር ላይ ስለሆነ ለዚህ የሚጠቅም ስልት መንደፍና Road map መቀየስ ይኖርበታል። ሂስ የሰነዘረውንና የተከራከረውን ሁሉ መሳደብ ቢቆም ጥሩ ነው። እሁን ይችን አስተያየት ስለሰጠሁ የሚሳደቡ እንደሚኖሩና ከኔ በላይ አማራ ነኝ የሚሉኝ እንደሚመጡ እጠብቃለሁ። የሚጠቅመው ነገር ላይ ሽንጥ ገትሮ መከራከረንና መማማርን በስድብ መተካት አይቻልም። ከፈቃደ ሸዋቀና fb_img_1479836743025

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *