ብአዴን ማን ነው ከፈቃደ ሸዋቀና

ብዓዴን ማን ነው? fb_img_1479836825605
============
ህወሓት ኢህአፓን ካጠፋ በኋላ ፊቱን ያዞረው እጃቸውን የሰጡት ወዶ ገቦችን አስልጥነን በፕሮግራማቸው ብሄረ አማራ የመሰሉ ነገር ግን ፀረ አማራ ሆነው እንድቆሙ ማድረግ አለብን ተብሎ በወቅቱ የነበሩ የህወሓት አመራር ስብሃት ነጋ፡መለስ ዜናዊ፡አረጋዊ በርሄ፡አባይ ፀሃይ፡ስዩም መስፍን፡አውአሎም ወልዱ፡አርከበ እቁባይ፡ስየ አብርሃ፡ገብሩ አስራት፡ጻድቃን ገብረተንሳይ፡ዘርአይ አስገዶም፡አስፍሃ ሃጎስና የህወሓቱ ምክትል ሊቀመንበርና የድርጅቱ ዋና አስተዳዳሪ ግደይ ዘርአጽዮን በዚህ አርእስት ላይ አጀንዳ ቀርቦ ሲወያዩ ምክትል ሊቀመንበሩ ግደይ ዘርአጽዮን ይህንን ሃሳብ አልቀበልም በማለት ራሱን አገለለ።የተቀሩት ውይይቱን ቀጥለው ስምምነት ላይ ደረሱ።ከላይ ከተዘረዘሩት የመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለቱ የህወሓት አመራር ተሰባስበውና ተወያይተው ስምምነት የደረሱበት ዋና ሃሳብ የአማራ ህዝብ ጠላታችን እንደመሆኑ መጠን በራሳችን ትዕዛዝና እንቅስቃሴ የሚታዘዝ ድርጅት ከፈጠርን አማራው ህልውናው የሚጠፋበት አማራጭ መንገድ ከዚህ የበለጠ ስለሌለን ፕሮግራሞቹን ጽፈን ሙሉ ቁጥጥር እያደረግን እነዚህን የኢህአፓ ወዶ ገቦች እናደራጅ ተብሎ ውሳኔ ተላለፈ።በዚህ ውሳኔ መሰረትም መለስ ዜናዊ፡ስብሃት ነጋ፡አባይ ፀሃዬ ለሚመሰረተው የአማራ ድርጅት ፕሮግራምና የቅድመ ሁኔታ ውይይት እንዲያዘጋጁ ሃላፊነቱ ተሰጣቸው።እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የህወሓት አመራር ያዘጋጁት ለህወሓት ፖሊት ቢሮ ስብሰባ ቀርቦ እነ አረጋዊ በርሄና ስዩም መስፍን አንድ ላይ ሆነው የቀረበውን ጽሁፍ አንብበው ፕሮግራሙ ላይ ተስማሙበት።ይህም በዋናነት እጃቸውን የሰጡ የኢህአፓ አባላት ውይይቱን የሚመሩ ሶስት ሆነው ወዶ ገቦቹን አሳምነው መስራች ጉባኤ ተካሂዶ ፕሮግራሙን አምነው ተቀብለው በህወሓት እርዳታ የአማራ ብሄር ድርጅት ተመስርቶ እንዲቋቋም ተብሎ ተወሰነ።
በፕሮግራሙ መሰረት የመወያያ አርእስቶች
ውይይቱ የተጀመረው ግንቦት መጨረሻ 1972 ሲሆን፣የውይይቱ መሪዎች መለስ ዜናዊ፡ስብሃት ነጋ፡አባይ ፀሃየ፡ሲሆኑ ተጠባባቂ ረዳቶች ደግሞ አውአሎም ወልዱና አርከበ እቁባይ ሆኑ።
የመወያያው ርዕስ
1. ነፃ ሃገር የነበረችው ኤርትራ ዛሬ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ስር ወድቃ ህዝቧ ለመከራና ለችግር ተዳርጓል።ከህዝባዊ ሓርነት ኤርትራ ጋር በመተባባር ኤርትራን ነፃ እናወጣለን፣
2 ነፃ ሃገር የነበረችው ትግራይ የራሷ መንግስትና መስተዳድር የነበራት ሃገር፣ከአፄ ዮሐንስ ሞት በኋል በምኒልክ ተወራ በአማራው ቅኝ አገዛዝ ቀንበር መውደቋ፣
3 የአሁኗ ኢትዮጵያ የታሪክ ድሃና ታሪክ የሌላት ሃገር፣በአፄ ምኒልክ የተመሰረተችና ከ100 ዓመታት ያነሰ ታሪክ ያላት ሃገር መሆኗን አምኖ መቀበል፣Ahmed Motuma
4 ምኒልክ ግዛቱን ለማስፋፋት በመነሳት ሳይወድ በግድ ኢትዮጵያዊነትን ተቀበል ተብሎ በአማራው የመንግስት ስርዓት በስቃይና በችግር የሚገኙት ብሄር በሄረሰቦች የራስን እድል በራስ በመወሰን እስከ መገንጠል አምኖ መቀበል። በዚህም ላይ ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች ወህኒ ቤት መሆኗን አምኖ መቀበል፣
5 አማራ የሚባለው ጨቋኝ ፀረ ሕዝብ መሆኑን አምኖ መቀበል
እነዚህ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱት ዋናውና የሚፈጠረው የአማራ ድርጅት የሚመራበት ፕሮግራም ሆነው ለውይይት ቀረቡ።
ይህንን ውይይት የህወሓት አመራር አባይ ፀሃዬ ሊቀመንበር፡መለስ ዜናዊ፡ስብሃት ነጋ ሆነው በመቅረብ ከሰኔ ወር መጀመሪያ 1972 እስከ ህዳር መጨረሻ 1973 ለ6 ወር ተከታታይ ውይይት ተካሄደበት፤በዚህ ጊዜም አዳዲስ የኢህአፓ አባላትም ሲቀላቀሉ ነበር።አብዛኛዎቹ ይህ ፕሮግራም ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሉአላዊነትና ፀረ-ሕዝብ ነው ይሉ ነበር።
የኢትዮጵያ ህዝብ በብዙ ሺህ ዘመናት የዳበረ ወንድማማችነት፣ኢትዮጵያዊነት፣በጋብቻ፣በባህል፣በእምነት በአንድነት ሆኖ ሃገሩን ኢትዮጵያን ከባእዳን ወራሪዎች ተከላክሎ ለኛ አስረክቦናል።በህዝባችን ያልነበረና ያልታየ ፕሮግራም ተሸክመን አንታገልም ሲሉ፣ ከፈቀዳችሁ ፕሮግራሙን ራሳችን ጽፈን ለአንድት ኢትዮጵያ፣ለአንድ ህዝብ እንዲታገል ፍቀዱ።አማራ የህዝብ ጠላት ነው የምትሉት እኛም አማራ ነን፡፡ኩሩውን አማራ የኢትዮጵያ የህዝብ ጠላት ነው ብላችሁ አትፈርጁት፣በማለት እልህና ንዴት እንዲሁም ብስጭት በተቀላቀለበት ለወራት ከተወያዩ በኋላ ተሰብሳቢው በሶስት ተከፈለ።
1. በህወሓት ፖሊት ቢሮ ተረቆና ተዘጋጅቶ የቀረበውን ተቀብላችሁ ታገሉ የምትሉንን አንቀበለውም። በአማራው ህዝብ እውቅናም ውክልናም አልተሰጠንም።አማራውን ብቻ መነጠል ጠባብ አስተሳሰብነው፣በዚህም ላይ አማራ ጠላት ነው እያላችሁን አማራውን ለክፉ ስቃይ አንዳርገውም።አማራ ኢትዮጵያዊ ነው፣ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ይታገል፣
2. ጊዜ ስጡን፣በረጋ መንፈስ አንብበን እና ተረድተን መልስ እንስጥበት የሚሉ፤
3. በህወሓት የቀረበልን ፕሮግራም ለብዙ ወራት ገንቢ ውይይት ያካሄድንበት ትክክለኛ የአቋም ፕሮግራም መሆኑን ስለአመንበት ካለምንም ተቃውሞና ጥርጣሬ ተቀብለነዋል ያሉ ናቸው።
ከዚህ ተከትሎ ምን ተፈጠረ የሚለውን ባጭሩ እንመልከት። እንደሁኔታው ተራ ቁጥሩ ይለዋወጣል።
ጊዜ ስጡን፣በረጋ መንፈስ አንብበን መልስ እንሰጥበታለን ያሉት፣ትንሽ ጊዜ ለማግኘትና ሕይወታቸውን ለማዳን የሚጠፉበትን እቅድ ማውጣት ላይ ተሰማሩ።ጋሻው ከበደ፤አያሌው ከበደ፣ምትኩ አሸብር ከማስታውሳቸውና ሌሎችንም ጨምሮ፣የተወሰኑት ወደ ሱዳን፣የተወሰኑት ደግሞ ለኢትዮጵያ መንግስት እጃቸውን በመስጠት ሕይወታቸን አዳኑ።አሁንም በሕይወት አሉ።
በህወሓት ፖሊት ቢሮ ተረቆ የተዘጋጀውን ፕሮግራም አንቀበልም ያሉት በህወሓት አመራር ላይ ጭንቀት ስለፈጠረበት የተወሰኑ አመራር ተሰብስበው፣ስብሃት ነጋ፣አባይ ፀሃየ፣ስየ አብርሃ፣መለስ ዜናዊ፣አውአሎም ወልዱ፣አርከበ አቁባይ፣ጻድቃን ገ/ተንሳይና ስዩም መስፈን ተሰብስበው እነዚህን የህወሓት ሃሳብ ያልተቀበሉትን አፈንጋጭ በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጡ።በውሳኔው መሰረት በስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ሃላፊነት እንዲፈጸም ተወሰነ።በዚህ ጊዜ ሃለዋ ወያነ (06) ብዙ እስረኞች ሞትን የሚጠባበቁ ስለነበሩ፣የቦታው ርቀትን ጨምሮ ሃሳቡ ቀርቦ ከህዝብ ግንኙነት አባላትም ተጨምረው ግድያው እንዲፈጸም ተደረገ።
ግደያውን የሚያስፈጽሙት፣ብስራት አማረና ሃሰን ሹፋ እንድሆኑ ፖሊት ቢሮው ወሰነ።
፩ ከወርዲ ሃለዋ ወያነ በአበበ ዘሚካኤልና ዘርአይ ይህደጎ የሚመሩ ተጨማሪ ፭ ታጋዮች
፪ ፃኢ ሃለዋ ወያነ በወልደሥላሴ ወልደሚካኤልና በተስፋየ መረሳ (ጡሩራ) የሚመሩ ፭ ታጋዮች
፫ ከህዝብ ግንኙነት
ለኡል በርሄ፣አብያ ወልዱ፣ሃይሉ በርሄ፤ቢተው በላይና ወልደ ገብርኤል ሞደርን።ሁሉም ተሰብሰበው ተንቤን ውስጥ አምበራ መጡና ገቡ።ግደያውን የሚፈጽሙት ብስራት አማረና ሃሰን ሹፋም መጥተው ከእነ ታምራት ላይኔ ጋር ቆዩ።ስብሃት ነጋም መጣና ከነብስራት አማረ ጋር ተነጋገረ።እነታምራት ላይኔ፣በረከት ስምኦን ወዘተ ከነበሩበት ቤት ራቅ ባለ ቦታ የመረሸኛ ጉድጓድ ተቆፍሮ ተዘጋጅቷል።እነዚህ በህወሓት የተረቀቀውን ፕሮግራም አንቀበለም ያሉት ቁጥራቸው በርካታ ነው።ስብሃት ነጋ ለልዩ ስብሰባ ብሎ በሃለዋ ወያነ አባላት ታጅበው ሄዱ።አባላቱ እጃቸውን በገመድ ጠፍረው በማሰር ወደ ተዘጋጀው መግደያ ጉድጓድ ወስደው በጥይት ደብድበው ገደሏቸው።ሁሉም አማራ ሲሆኑ፣ሃይላይ የሚባል አንድ የትግራይ ልጅ ከነሱ ጋር ነበር።
በህወሓት የተረቀቀውን ፕሮግራም አምነን ተወያይተን ገምቢ ፖሊሲውን ተቀብለናል ያሉት እነዚህ ናቸው፣
1. ሙሉአለም አበበ፣ አማራ
2. ሃይለ ጥላሁን፣ ትግራይ፣ እድገቱ ጎጃም
3. ታምራት ላይኔ፣ ከንባታ
4. ዮሴፍ ረታ፣ ትግራይ፣ ኤርትራ
5. በረከት ስምኦን፣ ኤርትራ
6. አዲሱ ለገሰ፣ ሂርና ሃረር
7. ህላዊ ዮሴፍ፣ ኤርትራ
8. ተፈራ ዋልዋ፣ ሲዳማ
9. ታደሰ ካሳ፣ ትግራይ
10. ለሰ ጥላሁን፣ አማራ፣ ትግራይ
11. ሲሳይ አሰፋ፣ ትግራይ
12. ኢያሱ በላቸው፣ ትግራይ፣ አማራ
ብአዴንን ማን ፈጠረዉ?እውነት የአማራውን ህዝብ ይወክላል?ብአዴንን ማን ነዉ የአማራ ህዝብ ተወካይ ያደረገዉ? ከየትስ መጡ?ለዚህ ሁሉ መልስ ግን ይህ ፅሁፍ ሙሉ መልስ የሚሰጥ ነው። ብአዴን በህወሓት የተፈጠረ ፀረ አማራ ድርጅት ነዉ አራት ነጥብ አለቀ። ይህ ለአማራ ህዝብ የሞት ሞት ከውርደትም ውርደት ነዉ!

*- ኢህዴን/ብአዴን ከምስረታው 1973 ጀምሮ እስከ 1983 ዓ.ም*

• 100% ቀለብ፣ትጥቅና ማንኛውም የሚያስፈልገውን ነገር የሚያገኘው ከህ.ወ.ሓ.ት ነበር፡፡ ለአንድ የህ.ወ.ሓ.ት ታጋይ 500 ግራም ቀለብ የቀን ራሽን የነበረ ሲሆን ለአንድ የኢህዴን/ብአዴን ታጋይ ደግሞ 800 ግራም ዱቄት የቀን ቀለብ ተመድቦለት ነበር፡፡ በአመትም ሁለት የወታደር ልብስ ይሰጠው ነበር፡፡
• 98% ወታደራዊ ስልጠና የሚያገኘውም ከህ.ወ.ሓ.ት ነበር- ከምስረታው እስከ መጨረሻዋ ሰዓት
• የመጓጓዣ ግልጋሎትም 100% ከህ.ወ.ሓ.ት ነበር የሚያገኘው፡፡ ከ1977 ረሃብ በኃላ በተለይም በ1980ዎቹ ህ.ወ.ሓ.ት በርካታ ተሸከርካሪዎች ሲኖሩት ኢ.ህ.ዴ.ን ግን ምንም አልነበረውም፡፡የነዳጅና ሌላ ሌላ ወጪም ሙሉ በሙሉ በህ.ወ.ሓ.ት የሚሸፈን ነበር፡፡
• የኢ.ህ.ዴ.ን የውጪ ጉዞ ወጪም 100% በህ.ወ.ሓ.ት የሚሸፈን ነበር፤ብቻ 100 በ100 የህ.ወ.ሓ.ት ጥገኛ ነበር፡፡ሌላው የሚገርመው ነገር 1983 ዓ.ም ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አዲስ አበባ ሲቆጣጠር የነበረው የሐይል ሚዛን ነው፡፡ህ.ወ.ሐ.ት አዲስ አበባ ሲገባ መደበኛ ሰራዊት፣አዲስ ምልምሎች፣የአካባቢ ሚሊሻዎች፣ሲቪል አጋር ሁሉም ተደምሮ 223 ሺህ ገደማ ሃይል ነበረው፡፡ኢ.ህ.ዴ.ን ደግሞ ጠቅላላ 4500 ብቻ ነበረው፡፡ከዚህም በመደበኛነት ውጊያ ላይ የነበረው 300 ሰው ብቻ ነው!
ብአዴኖች አሁንም 36ኛ አመታቸዉን ለማክበር ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ መድበዋል፤አመት በመጣ ቁጥር ጆሮ የሚኮረኩር ዘፈናቸዉን መልቀቅ ጀምረዋል።እንዳያልፉት የለም! ያ ሁሉ ታለፈ፤ታጋይ የህዝብ ልጅ በደሙ በላቡ ደማቅ ታሪክ ፃፈ።ብአዴን አይደለም ታግሎ በደሙ በላቡ ደማቅ ታሪክ ሊፅፍ ይቅርና በብዙ መልኩ ምንም አቅም ያልነበረውና የሆነ ሃይል እፍ ቢልበት ድርግም ብሎ ሊጠፋ የሚችል ሃይል ስለነበር ህወሓትም የኢህዴን/ብአዴን በህይወት መዝለቅ አስፈላጊነት በመረዳት እዳይሞት እንዳይከፋው ጠብቆና ተንከባክቦ በርካታ ጠባቂ ተመድቦለት፣ ስንቅም ምንም ሳይጓደልበት፣የተኩስ ድምፅም እምብዛ ሳይሰማ አዲስ አበባ የደረሰ ቡድን ነው፡፡ በአጠቃላይ ብአዴን ወታደራዊ ሚናዉ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ፖለቲካዊ ሚናዉ ግን እጅግ በጣም የጎላ ነበር።

*ብአዴን ከህወሓት የተሰጠዉ ተልዕኮ*

1 የትግራይ አዋሳኝ የሆኑ የጎንደርና የወሎ መሬቶች ወደ አባይ ትግራይ ወይም ታላቋ ትግራይ ካርታ እንዲካለሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት

2 ሰፊዉን የአማራ ህዝብ ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ ከፍተኛ ጫና በማሳደር በተዛባ የመረጃ አቅርቦትና በዉሸት ፕሮፓጋንዳ ማደናገር

3 በወሊድ መቆጣጠሪያ ስበብ የአማራን ሴቶች በማምከን የአማራን ህዝብ ቁጥር እንድቀንስ ማድረግ

4 የአማራ ባለሃብቶችን ማዳከም

5 ወያኔ አማራ ክልል ብሎ ከከለለዉ ክልል ዉጭ የሚኖረዉ አማራ ተለይቶ እንድፈናቀልና ከአማራ ክልል ዉጭ ያለዉ አማራ ሰርቶ እንዳይበላና የመኖር መብቱ እንድነፈግና እንደ ውጭ ዜጋ እንድታይ በአማራ ህዝብ ተወካይ ስም ለኦህዴድና ለደኢህዴን ካድሬዎች ፈቃድ መስጠት

6 በአማራ ክልል የሚገኙ የገጠርም ሆኑ የከተማ ቁልፍ ቦታዎች ለወያኔ አባላት ንብረት እንድሆኑ በማድረግ ሰፊዉን የአማራ ህዝብ በድህነት አሮንቃ ውስጥ እንዲዘፈቅ ማድረግ

7 የአማራን ህዝብ ታሪክ ጥለሸት መቀባት፣ባህል መበረዝና ታሪካዊ ቅርሶችን ማጥፋት

8 ኢህአዴግን የሚቃወሙ የአማራ ወጣቶችን መደብደብ፡ማሰር፡በቶርቸር ማሰቃየት፡መግደልና ሀገር ጥለዉ እንድሰደዱ ማድረግ
Yared Birhanu Yared Tilahun ህብረብሔር ሰለሙን ብርሃነ ኣቦይሓጎስ ስለ ሁሉም እግዚአብሔርይመስገን ሰበርዜና ሰው አለበልቤ AbegaCool AndmTachgaint Dehana WoredaAndm LogOut Bass Asnake Bassoliben Youthleague Basso Worda ተንታ ኮሙኒኬሽን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *