የሕወሃት ኮማንድ ፖስት በመከላከያ አባላት ላይ የግድያ እርምጃ እየወሰደ ነው

የሕወሃት ኮማንድ ፖስት በመከላከያ አባላት ላይ የግድያ እርምጃ እየወሰደ ነውfb_img_1479745760132

በልኡል አለም
በጄኔራል ሲራጅ ፈርጌሳ የሽፋን ስእል ተሰጥቶት በጄኔራል ሳሞራ የኑስ የበላይነት ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የወታደራዊ ደህንነት የመከላከያ ሰራዊቱ ላይ አደገኛ እርምጃ በመዉሰድ ላይ አተኩሯል።
በመሆኑም ያለ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ኮማንድ ፖስቱ በስዉር እንዲያጠቃ ትእዛዝ ተላልፎለት የኮማንድ ፖስቱ ደህንነትን ተገን ያደረገዉ ዉሳኔ በ8 የመከላከያ አባላቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በማዘዙ፣ ትናንት በ11/03/2009 በመላዉ ሐገሪቱ የተነሳዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት ይደግፋል ያደራጃል የተባለዉ የመካከለኛዉ እዝ ባልደረባ የም/መቶ አለቃ አለበል ትእዛዙ የዉሳኔዉ ሰለባ ሲሆን በተጨማሪ ከሰሜን እዝ ወታደራዊ መምሪያ ክፍል ወታደር ቅጣው ቢያድግልኝ ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ወታደር ቅጣዉ ቢያድግልኝ ሐሙስ ከሰሜኑ እዝ ክፍለ ጦር መምሪያ ትፈለጋለህ ተብሎ ከተወሰደ በኋላ በጥይት ተደብድቦ መረሸኑን የአይን እማኝ የነበሩ የሰራዊቱ አባላቶች በከፍተኛ ቁጭት ለምንጫችን ተናግረዋል።
በመረጃ አጠባበቅና ፍልሰት ላይ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት እንደነበረዉ ተረጋግጧል የተባለዉ የም/መቶ አለቃ አለበል ትእዛዙ በኮማንድ ፖስቱ ስዉር ደህንነቶች ሆን ተብሎ በተቀናበረ የመኪና አደጋ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።
የመከላከያ ምንጮች እነደገለጹት ሌሎች ስድስት የሰራዊቱ አባልት ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወሰድ የትእዛዝ ሰነድ የወጣ ቢሆንም መረጃዎች ቀድመዉ በማፈትለካቸዉ ስድስቱም የሰራዊቱ አባላት እነደተሰወሩ ለመረዳት ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *