የአዲስ አበባው ደህንነት ቢሮ ተዘረፈ።ሕወሓት በመጨረሻው ሰዓት ማሟጠጥ ይዛለች።

የአዲስ አበባው ደህንነት ቢሮ ተዘረፈ።ሕወሓት በመጨረሻው ሰዓት ማሟጠጥ ይዛለች።

አዲስ አበባ ከኣፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ጀርባ በቅርብ ርቀት ከሚገኘው የደህንነት ቢሮ ውስጥ 14 ሚሊዮን ዶላር መዘረፉን የውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ተናግረዋል፤ ምንጮቹ እንዳሉት ላለፉት ሶስት ኣመታት ከኣየር መንገድ ከፖሊስ ኢግዚቢት እንዲሁም ከኮንትሮባንድ ተይዘው በኣዲስ ኣበባ ደህንነት ቢሮ የተከማቹ ዶላሮችን የዘረፈው ኣካል ማን እንደሆነ ኣልታወቀም ሲሉ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል።
በኦሮሚያና ኣማራ ክልል ተቃውሞ ከተነሳ ጀምሮ ለስብሰባዎችና ለጉዳይ በሚል ሃያ ኣራት ሰኣት የሕወሓት ባለስልጣናት እንደሚመላለሱ ሲታወቅ እነዚህ ባለስልጣናት በሚሰበሰቡበት ለሊት በኣከባቢው ጥበቃ የሚያደርጉት ልዩ የደህንነት ሃይሎች ሲሆኑ ሌሎች ወደ ቢሮው እንዳይደርሱ እንደሚደረግ እና እረፍት እንደሚሰጣቸው ታውቋል ሲሉ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ይኸው ቢሮ መዘረፉ ሲታወቅ የሕወሓት የደህንነት ባለስልጣናት በየግላቸው የሚመሯቸው ማፊያ ቡድኖን ያሏቸው ሲሆን ምናልባት እንደባለፈው ዘረፋው በቡድኖቹ የጋራ ቅንጅት ተተግብሮ ይሆናል ሲሉ ምንጮቹ ኣክለው ሲገልጹ በባለፈው የቤተ መንግስቱ ተኩስ በሕወሓት ጄኔራሎች ተገደለ የተባለው የደህንነት ሚኒስትሩ በሕይወት ያለ ሲሆን የማፊያ ስራውን በመስራት ላይ ሲገኝ የደህንነት ሚኒስትሩ ተገደለ የሚለው የሃሰት ዜና በደህንነቶች የተፈበረከ ውዥንብር መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል። ከምንሊክ ሳልሳዊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *