አይዛቹ አትሞቱም የሁላቹሁም እትብት የተቀበረው በክልል በረት ውስጥ ሳይሆን በኢትዮጵያ መሬት ውስጥ ነው።

የመለስ እራይ ወራሹ ሀይለማርያም ደስአለኝ የሰውን ልጅ እያሳደደ የሚገለውን የናዚ ስርአት እራዮን ለማስፈፀም የሞት መንፈስ ከተሸከመ ጀምሮ ስንቱን ንፁሀን ዜጉችን በአጋዚ ጥይት አሳጨዳቸው ብዙሀኑን ህዝባችንን አስገደለ በአልሞት ተጋዳዮ የዘር ልክፍት ባለባቸው አጋዝያን እያስረሸነ እንደሆነ ይታወቃል። የሀይለማርያም እራይ አስፈፃሚ የህዝብን ድምፅ ላለመስማት ጆሮውን ዘግቶ የሚሰሩት አሻጥርና ሴራ ሴጣን እራሱ አያውቀውም! የትግራይን ህዝብ ካማራ ክልል ወያኔ የወከላቸው የብአዴን ቅጥረኞች መቀሌ ድረስ በመላክ በአማራ ህዝብ ስም የትግራይ ነፃ አውጪ ብድን ለሰራነው በደል ይቅርታ የሚል በቪድዮ አስቀርፀው በአማራ ፅረ ሰላም የተፈናቀሉትን ትግራዊያንን የአማራ ህዝብ በተወካዮቹ አማካይነት ይቅርታ ጠይቋል ብለው ትልቅ ዘመቻ ላይ መሆናቸውን አይተናል የሱማሌው በበረት የታጠረው ክልልም የሱማሌ ህዝብን በረሀብ የጨረሰ ጫት ቃሚ ድልብ መሀይም በምርቃና ተነስቶ ያለነሱ መኖር እንደማይችል ስለሚያውቀው ታማኝነቱን በሚገባ አስመስክራል ማን ስልጣን ሰጠውና
አስር ሚሊዮን ብር ከአማራ ክልል በአባይ ወልዱ ለተፈናቀሉት
10 ትግራዮች 10 ሚሊዮን ብር መልሶ ማቋቋሚያ ከሱማሊያ የክልል በረት ተሰጠ በሚል የተሰራውም ድራማ አለም ላይ ያለ ኢትዮጵያዊ በመገረም ተመልክቶታል። ከጉራ ፈረዳ አማራ ሲፈናቀል እየተገደለ ወደ ሀገራቹ ሂዱ ሞፈር ዘመት ናቸው ደኑን አቃጥለው ከሰል እደረጉት በሚል መለስ ያፈናቀላቸው የእግዜር ፍጡሮች ተፈናቅለው ደብዛቸው እንዳይገኝ አድርገው ሲያጠፋቸው አይተናል… አባይ ወልዱም ተባረሩብኝ ያላቸውን ካድሬወች በሰራው ስራ በመኩራራት መቀሌ ላይ ታላቅ የመሞጋገስ ምሽት ተከናውናል።ይህ የናዚ ስርአት ለማፍረስ ትግሉና አመፁን ባለስልጣኖቹ ጋዳ ማስገባት ምንም ጥያቄ የሌለው ጉዳይ ነው በተለይ ስብሰባ ሲጠሩ በስብሰባ የሚመጣ ለውጥ እንደሌለ ሀያ አምስት አመት የታየ ጉዳይ ነው ትግል ነውና ትግሉ ከዚህ በላቀ ደረጃ መምረር ግድ ይላል። ገዱ እና ካለምነ ምላስ ምን አልተገኝም የአዞ እንባ አለቀሱ ይትግላችን መፍቴሄ አይደለም ሊሆንም አይችልም።
የናዚ ወያኔን የከፋፍለክ ግዛ ስርአት ለመገርሰስ ከስልጣን ለማስለቀቅ በሚደረገው ግብግብ እስከዛሬ ከተደረጉት ተጋድሎውች ትግሉ እቅጣጫውን በመቀያየር ታሪክ መስራት እንደሚቻል ተመልክተናል የህዝብ አልገዛም ባይነት fb_img_1475922440895እስከሞት ድረስ አድርሶታል የውያኔ ንብረቶች ዶግ አመድ ሆነዋል እሁንም ይቀጥላል ወያኔወች ይህችን የቀለም አብዮት በምን አይነት ሊቆጣጠራት አይቻላቸውም ይህ እሳት የዘመናት ባርነትን ላለመቀበል የሚደረግ ተጋድሎ በመሆኑ በሁሉም አቅጣጫወች የኢትዮጵያውያን ተጋድሎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ግዜ የማይሰጠው ጉዳይ ሰለሆነ ሞያ በልብ ነው እንላለን ባለስልጣኖችን የማስወገድ ሴራ ይጎንጎናል ያለመሰዋትነት ነፃነት የለም ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርምና የወያኔ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ድር ቢያብር አንበሳ ያስረነውና በወያኔ ላይ የተጀመረው የነፃነት ትግል ይፋፋማል ማንም አያስቆመውም
በመጨረሻ ሳልናገር የማላልፈው ነገር እናተ ዲያስፖራ ያላቹ ወገኖቻችን በክልል በረት ባትጠራሩ ምንኛ ደስ ባለን የአማራ ፖሮቴስት የኦሮሞ ፖሮቴስት እያላቹ ወያኔ በበረት ያጠራቸውን ህዝቦች እናተም ደግማቹ አትጠራቸው አይዛቹ አትሞቱም የሁላቹሁም እትብት የተቀበረው በክልል በረት ውስጥ ሳይሆን በኢትዮጵያ መሬት ውስጥ ነው። 25 አመት በበረት ተከፋፍለን የኖርነው ይበቃናልና አናተ ያገራችን ውጪ ያለከው ዲያስፖራ ወገናችን ሆይ አይምሮክ ይስራ ገዳዮቻችን ይህችን ቃል ፈፅሞ ያማቸዋልና ያስጮሀቸዋል ያፈራግጣቸዋል የአንድነትክ ዜማ ጌታቸው እረዳን ከፍ ዝቅ አድርጉታል ተጠቀመው 666 ናዚን ማርከሻ እንደፀበልክ ነውና አይዞክ አንተን አይፋጅክም ለእነሱን ግን ይህ ቃል እሳት ነውና ሀይል አለው ያስለፈልፋል “የኢትዮጵያ አመፅ እያልክ” ትጮህ ዘንድ ካለንበት መልእክታችን ይድረስክ!!!!!!!
ተክለ እስጢፋኖስ ከአዲስ አበባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *