ቀድሞ የወጣው የስብሰባው ይዘት እና ቀጣዩን የኦሮሞ ሕዝብ ትግል አስመልክቶ የተነገረ ንግግር ብዙዎች ላይ ጥያቄና ጥራጥሬ አጭሯል::

የኦሮሞ ልሂቃን ከኀዳር 2-4 በአትላንታ ይሰበሰባሉ:: ስብሰባው የኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ በትንሿ ጊንጪ ዳግም የተቀሰቀሰበት አንደኛ ዓመት በሚከበርበት ጌዜ ይሆናል (የኦሮሞ ተቃውሞ በመጋቢት ወር 2006ዓም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ መጀመሩ ይታወሳል)
ቀድሞ የወጣው የስብሰባው ይዘት እና ቀጣዩን የኦሮሞ ሕዝብ ትግል አስመልክቶ የተነገረ ንግግር ብዙዎች ላይ ጥያቄና ጥራጥሬ አጭሯል::
ገዢው ስርዓት ህወሓትም በፍጥነት ልሳኖቹ በሆኑት የመንግሥት ሚዲያዎች እና ካድሬዎች ለፕሮፓጋንዳ ተጠቅሞበታል:::
የአሮሞ ልሂቃን ለብቻ መሰብሰብ በመላው ኢትዮጵያ ለተንሰራፋው ቀውስ መፍትሔ ይሆናል ወይ?

የነፃነት ቻርተር ሲነሳ በቀዳሚነት የሚጠራው የደቡብአፍሪካው ተቃዋሚ ፓርቲ ኤ.ኤን.ሲ በ1953 ያወጣው የነፃነት ቻርተር ነው::

ቻርተሩ ሀገር አቀፍ እና ዘር ቀለም ሳይለይ ለመላ ሀገሪቱ የተሰናዳ ብሔራዊ ጥሪ ነበር::
የኦሮሞ ልሂቃን አትላንታ ላይ የሚያዘጋጁት ሌላውን ያካተተ አይደለም:: ለምን?
ፕሮፌሰር እዝቂኤል ገቢሳ መልስ ይሰጣሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *