ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከሰጡት መግለጫ የተቀነጨበ

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከሰጡት መግለጫ የተቀነጨበ

“የሕዝብ አመጽ በተደራጀ መንገድ እንዲካሄድና ለትግሉም የሚያስፈልገውን አቅርቦት በማዘጋጀት በኩል ለአመጽ fb_img_1475760649157ከተደራጀነው ኃይሎች የሚጠበቀውን ሁሉ እንደምናደርግና እያደረግንም እንደሆነ እንዲታወቅ እንፈልጋለን። የዚህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች እንዲስፋፋ ለማድረግ እየሠራንበት ያለው አብይ ሥራችን ነው። በዚህ መስክ የሚደረገው እንቅስቃሴ ዝግጅቱን በቶሎ አጠናቆ ሊደበቅ በማይችልበት ሁኔታ በግልጽ የሚወጣበት ግዜ ሩቅ እንዳልሆነ አረጋግጥላችኋለሁ። ይህ እንቅስቃሴ ብዙ ሕይወት ሳያስገብር ከዳር እንዲደርስ በወያኔ ስር ተጠርንፎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወታደር አሁንም በትንሽ በትንሹ እንደጀመረው በሰፊው ተንቀሳቅሶ ከሥርዓቱ ጋር ሳይሆን ከሕዝቡ ጎን እንዲቆም የምናደርገው ጥረትም ተጠናክሮ ይቀጥላል።”

ሙሉ መግለጫው እንዳለቀ ይቀርባል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *