የዞን7 ጦማርያን ዳግም በወያኔ ካድሬወች ታፈኑ!

የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ (Natnail Feleke) ፣ ፀደቀ ድጋፌ (Tsedeke Digafie) እና አዲስአለም ደስታ በሁከት ማነሳሳት ወንጀል ተጠርጥረው በትላንትናው እለት ታስረዋል፡፡ ትላንት ከስራ ሰዓት በኋላ በላሊበላ ሬስቶራንት ተገናኝተው ሻይ ቡና እያሉ በሚጨዋወቱበት ወቅት ነው ከምሽቱ 1፡30 ላይ እዛው ሬስቶራንት በነበሩ ሲቪል የለበሱ የፓሊስ አባላት ተይዘው 6ኛ ፓሊስ ጣቢያ የታሰሩት፡፡ ዛሬ ጠዋት ላይ ሶስቱም ቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን የቀረበባቸው ክስ “ላሊበላ ሬስቶራንት ሆነው መንግስት በቢሾፍቱ የኢሬቻ አክባሪዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ትክክል እንዳልሆነ በዙሪያቸው ያሉትን ሰዎች ለተቃውሞ እንዲነሳሱ በሚያደርግ መልኩ ሲያወሩ ነበር “ የሚል ነው፡፡ በዋስትና እና ምስክሮች ጉዳይ ላይ ምላሽ ለመስማት ነገ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ቄራ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *